ትንናት ለሊቱን አል - ሻባብ የ19 ሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት ማጥፋቱንና ቀለብ ጭነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከባድ የጭነት መኪናዎችንም ማጋየቱን የሶማሊያ መንግሥታዊ ዜና ኤጀንሲዎች አስታወቁ።
እስላማዊ ቡድኑ ጥቃቱን የፈፀመው በማዕከላዊ ሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ በሆነችው ሂርሻቤሌ አስተዳደር ሂራን አካባቢ ነው።
ከባድ የጭነት ተሽካርካሪዎቹ ጥቃት የደረሰባቸው የእርዳታ የምግብ አቅርቦቶችን ከባላድዌይኔ ወደ ማሃስ ከተማ ይዘው እየሔዱ ሳለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የአካባቢው አረጋዊ ፋራህ ኤደን ጥቃት ፈፃሚዎቹ ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውንና ወደ ማሃስ ሲሄዱ የነበሩ ከባድ የጭነት መኪናዎችን ማቃጠላቸውን ሲገልጡ፤ መንግሥታዊው ሶና የዜና ኤጂንሲ በበኩሉ የአል - ሻባብ ተዋጊዎች ወደ ማሃሳ የእርዳታ ቀለብ ይዘው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎችን እንዳጋዩና በጭነት መኪናዎቹ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ሰላማዊ ሰዎችንም መግደላቸውን ዘግቧል።
የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሃሰን ሼክ ማኅሙድ ጥቃቱን አውግዘዋል።
ከሁለት ሳምንታት በፊት አል ሻባብ ሞቃዲሾ ያለውን ሃያት ሆቴል ለ30 ሰዓታት ተቆጣጥሮ 21 ሰዎችን ገድሏል፤ 117 ሰዎችን ለቁስለኝነት ዳርጓል።
ጎርቫቾብ
በሺህዎች የሚቆጠሩ በመጨረሻው የሶቭዬት ኅብረት ፕሬዚደንት ሚክኻይል ጎርቫቾብ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ስንብት ፈፀሙ።
በ91 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ጎርቫቾቭን ለቀስተኞች ክፍት የሆነው የአስከሬን ሳጥን ውስጥ እንዳሉ ተሰልፈው በተራ ገሰናብተዋል።

Mourners attend a memorial service for Mikhail Gorbachev, the last leader of the Soviet Union, at the Column Hall of the House of Unions in Moscow, on September 3, 2022. Credit: EVGENIA NOVOZHENINA/POOL/AFP via Getty Images
በሌላም በኩል የሩስያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን በሥራ በመጠመድ ሳቢያ በጎርቫቾቭ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ አልተገኙም። ሆኖም ጎርቫቾቭ እንዳረፉ በሆስፒታል ተገኝተው አበባ ማኖራቸው ተነግሯል።