እንግሊዝና ሲኔጋል በኳታር የፊፋ ዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ግጥሚያ በእንግሊዝ ረቺነት 3 ለ 0 ተለያይተዋል።
እንግሊዝን ከፈረንሳይ ጋር ለቀጣዩ ሩብ ፍፃሜ ፍልሚያ ለመግጠም ያስቻሉትን ግቦች ያስቆጠሩት ጆርዳን ሄንደርሰን 38' ሃሪ ኬይን 45+3' ቡካዮ ሳካ በ37ኛዋ ደቂቃ ሶስተኛዋን ግብ በማስቆጠር ነው።

ቀደም ሲል በተከናወነው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ፈረንሳይ ፖላንድን 3 ለ 1 በማሸነፍ ለሩብ ፍፃሜ ውድድር አልፋለች።
የጥሎ ማለፍ ግጥሚያ ሠንጠረዥ
ጃፓን እና ክሮኤሽያ (ማክሰኞ ዲሴምበር 6 / ሕዳር 27) 2:00 am [AEDT]
ሞሮኮ እና ስፔይን (ረቡዕ ዲሴምበር 7 / ሕዳር 28) 2:00 am [AEDT]
የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ ሠንጠረዥ
ኔዘርላንድስ እና አርጀንቲና (ቅዳሜ ዲሴምበር 10 / ታሕሳስ 1) 6:00 am [AEDT]
እንግሊዝ እና ፈረንሳይ (እሑድ ዲሴምበር 11 / ታሕሳስ 2) 6:00 am [AEDT]

