በመሳሪያ የተቀነባበሩ አልበችሞን በማሳተም እንዲሁም በርካታ መድረኮች ላይ የሙዚቃ መሳሪያ በመጫዎት ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈው የአንጋፋው ድምፃዊ ጋሽ ፍሬው ኃይሉ ልጅ ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው ለሥራ በሄደበት ጣሊያን ሮም ትላንት ምሽት በአረፈበት ሆቴል ሕይወቱ ማለፉ ተነግሯል ።
ሙዚቀኛው በኢትዮጵያ ኤምባሲ በጣሊያን ሮም ከተማ ሥራዎቹን አቅርቦ ወደ አረፈበት ሆቴል ከገባ በኋላ ምክንያቱ ለጊዜው ባልታወቀ ሁኔታ ማረፉን የጣሊያን ፖሊሶች መናገራቸው ተዘግቧል።
በጣሊያን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና የሙያ አጋሮቹ ከአገሪቱ ፖሊስ ጋር ተነጋግረው የአርቲስቱን አስክሬን በአገሩ ለማሳረፍ እንቅስቃሴ መጀመራቸውም ታውቋል::
ዳዊት ፍሬው የክላርኔት የሙዚቃ መሳሪያውን እየተጫወተ የሠራው ሶስት የሙዚቃ አልበም ያለው ሲሆን የአንጋፋው ድምፃዊ ፍሬው ሀይሉ ልጅም ነው።