ኢሰመኮ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል የሚያደርግ የባለሙያዎች ቡድን አሰማራ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ጋር ተያይዞ ሰዎች ለሚገጥሟቸው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በነፃ የስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወል መረጃና ጥቆማዎችን ማድረስ እንደሚችሉ ዳግም ጥሪ አቅርቧል።

Referendum.jpg

Credit: NEBE

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሚገኙ ስድስት ዞኖች (ጋሞ፣ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ) እንዲሁም አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ አማሮ፣ ባስኬቶ፣ ዲራሼ እና አሌ) በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታ በሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የሚከታተል የባለሞያዎች ቡድን ወደ ስፍራው ማሰማራቱን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ለመተባበር እና ኃላፊነቱን ለመወጣት ከቦርዱ ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙን አስታውሶ፤ የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ቡድኖች በሚሰማሩባቸው አካባቢዎች በሕዝበ ውሳኔ የድምፅ መስጫ ዕለት እና ከዚያ በኋላ ባሉት ቀናት በሕዝበ ውሳኔ ጣቢያዎች በመገኘት ምልከታ ያደርጋሉ፤ ድምፅ የሚሰጡ ሰዎችን፣ የሕዝበ ውሳኔ አስተባባሪዎችን፣ የጸጥታ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ታዛቢዎችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ሚና በመመልከት ክትትል በሚያደርጉባቸው የሰብአዊ መብቶች ላይ መረጃዎችን እንደሚያሰባስቡ አመላክቷል።

ኢሰመኮ ማንኛውም ሰው እና ተቋማት በሙሉ ኮሚሽኑ ላሰማራቸው የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ቡድን አባላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ ከሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ጋር ተያይዞ ሰዎች ለሚገጥሟቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በነጻ የስልክ መስመር 7307 ላይ በመደወልም መረጃ እና ጥቆማዎችን ማድረስ እንደሚችሉ ዳግም አሳስቧል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ ሕዝበ ውሳኔ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚስተናገዱበት እና ዜጎች በሕዝባዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብታቸውን የሚተገብሩበት አንደኛው ሂደት መሆኑን አስታውሰዋል።

አክለውም “ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በተከናወኑ ሕዝበ ውሳኔ ባደረገው ክትትል ግኝቶች መሠረት ሰዎች የፈለጉትን የፖለቲካ አመለካከት በነጻነት የመያዝ እና የመግለጽ እንዲሁም ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ የድምፅ አሰጣጥ

ሂደት የመምረጥ መብቶቻቸውን እንዲተገብሩ ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤ ዜጎች ያለምንም መድሎ፣ ጫና እና ጣልቃ ገብነቶች በነጻነት ድምፅ መስጠት እንዲችሉ ሁሉም አካላት ግዴታቸውን እንዲወጡ” ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ኢሰመኮ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል የሚያደርግ የባለሙያዎች ቡድን አሰማራ | SBS Amharic