እንግሊዛውያን የንጉሥ ቻርልስ ሳልሳዊ በዓለ ሲመትን በክብረ በዓል ቀንነት አክብረው እንደሚውሉ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ተገለጠ።
የ73 ዓመቱ የእንግሊዝ ንጉሥ በዓለ ሲመት የሚከበረው ሜይ 6 ቀን 2023 / ሚያዚያ 28 ቀን 2015 ሎንዶን በሚገኘው ዌስት ሚኒስትር ቤተፀሎት ነው።
ፈረንሳይ
የፈረንሳይን ናሽናል ራሊ ፓርቲ ለአንድ አሠርት ዓመት በቀኝ ፅንፈኝነት የመሩት ሜሪን ለ ፔን በአዲስ ቀኝ ክንፈኛ መሪ ተተኩ።
አዲሱ ተተኪ ጆርዳን ባርዴላ ከ84 ፐርሰንት በላይ የፓርቲ አባላትን ድምፅ በማግኘት ሌሎች ተፎካካሪ ዕጩዎችን ድል መንሳት ችለዋል።
የ27 ዓመቱ ባርዴላ ከወዲሁ በአዲሱ ትውልድ አክራሪ የቀኝ ክንፍ መሪነት ተፈርጇል።