ሞሮኮና ስፔይን ዛሬ ማለዳ በኳታር የትምህርት ከተማ ስታዲየም ባካሔዱት የጥሎ ማለፍ ግጥሚያ ሞሮኮ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ለቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ለማለፍ በቅታለች።
ሞሮኮ ሶስቱን ግቦች ያስቆጠረችው በሙሉና ተጨማሪ 120 ደቂቃዎች ያለ ግብ አቻ በመውጣታቸው በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት ነው።
የ2010 የዓለም ዋንጫ ባለቤት የነበረችውን ስፔይንን ድል የነሳችው ሞሮኮ በዓለም ዋንጫ ውድድር ታሪኳ ለሩብ ፍፃሜ ስትበቃ ይህ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነው።
ከስፔይን የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት መቺዎችን ሰርጂዮ ባስኩዌትስ፣ ካርሎስ ሶሌር እና ፓብሎ ሳራብያ የተመቱ ኳሶችን መረብ ላይ እንዳያርፉ በመያዝ ቡድኑን ለድል ያበቃው ግብ ጠባቂ ያሲን ቦዩኑ የሞሮኮ አንፀባራቂ ኮከብ ለመሆን በቅቷል።

የፖርቹጋል ቡድን 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ስዊትዘርላንድ ድል ነስቶ ለሩብ ፍፃሜ አልፏል።

በቀጣዩ ሩብ ፍፃሜ ከሞሮኮ ጋር ለግማሽ ፍፃሜ ፍልሚያ ይቀርባል።
የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ ሠንጠረዥ
ብራዚል እና ክሮኤሽያ (ቅዳሜ ዲሴምበር 10 / ታሕሳስ 1) 2:00 am [AEDT]
ኔዘርላንድስ እና አርጀንቲና (ቅዳሜ ዲሴምበር 10 / ታሕሳስ 1) 6:00 am [AEDT]
ሞሮኮ እና ፖርቹጋል (እሑድ ዲሴምበር 11 / ታሕሳስ 2) 2:00 am [AEDT]
እንግሊዝ እና ፈረንሳይ (እሑድ ዲሴምበር 11 / ታሕሳስ 2) 6:00 am [AEDT]

