በግብፅ አደራዳሪነት ከእስላማዊ ጂሃድ ጋር የጋዛ ተኩስ አቁም ግብር ላይ መዋሉን እሥራኤል አስታወቀች።
በእስራሌልና ጋዛ በሚገኘው እስላማዊ ጂሃድ መካከል ለሶስት ተከታታይ ቀናት በተካሔደ ግጭት የሮኬት ውንጨፋና የአየር ድብደባዎች ተካሂደዋል።
በግጭቱ ሳቢያም 15 ሕፃናትን ጨምሮ 43 ያህል ሰዎች ተግድለዋል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።
የእስላማዊ ጂሃድ ባለስልጣን ዳውድ ሺሃብ በግብፅ አማካይነት የሼክ ባሳም አል ሳዲ እና ክሃሊ አዋዴህን ከእሥር የማስለቀቅ ቃል ተከትሎ በፍልስጤም በኩል ድርጅታቸው የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንደሚያከብር ገልጠዋል።
***
የአውስትራሊያ የሥራ ፍትሕ ኮሚሽን ለአረጋውያን ክብካቤ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ አስቧል።
ለሠራተኞቹ ምን ያህል የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ለኮሚሽኑ በሚቀርበው ምክረ ሃሳብ አዘል ደብዳቤ ላይ እንደሚገለጥ ተጠቁሟል።
የሌበር ሚኒስትር ታንያ ፒልበርስክ መንግሥት ለደመወዝ ጭማሪው የገንዘብ ድጎማ እንደሚያደርግና በሰዓት $22 ክፍያ ከሠራተኞቹ አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ተናግረዋል።