አንድ የስድስት ዓመት ተማሪ ዓርብ ዕለት መምህርቱን መማሪያ ክፍል ውስጥ ተኩሶ ማቁሰሉን የኒው ፖርት ኒውስ ክተማ ፖሊስና የትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች አስታወቁ።
ምንም እንኳ የስድስድት ዓመት ልጅ ሰውን ተኩሶ የማቁሰል ድርጊት ከዚህ ቀደም እንግዳ ባይሆንም እጅግም የተለመደ አለመሆኑን የመስኩ ተጠባቢዎች አመላክተዋል።
በፖሊስ ገለጣ መሠረት አደጋው ከደረሰበት የሪችኔክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንድም የቆሰለ ተማሪ የለም።
በስድስት ዓመቱ ተማሪ የቆሰለችውና በ30ዎቹ ዕድሜ ውስጥ ያለችው መምህርት የደረሰባት የመቁሰል አደጋ ብርቱ ሲሆን ከቀትር በኋላ ግና መጠነኛ መሻሻል ማሳየቱም ተነግሯል።
የስድስት ዓመቱ ልጅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ የኒው ፖርት ኒውስ ፖሊስ አዛዥ ስቲቭ ድሩ አስታውቀዋል።
ፍልሰተኞች
ከሊቢያ ወደ አውሮፓ በሜዲቲራኒያን ባሕር አቋርጠው ለማለፍ ሲሞክሩ የነበሩ 73 ፍልሰተኞች በድንገተኛ አደጋ ደራሽ ሠራተኞች ለትድግና በቅተዋል።
16 ወላጅ / ሞግዚ አልባ ልጆችን አክሎ 73ቱን ፍልሰተኞቹን እንደታደጉት ድንበር አልባ ሐኪሞች ምግባረ ሰናይ ድርጅት ገለጣ፤ ግለሰቦቹ ይጓዙ የነበሩት ሚዛኗን ባልጠበቀችና ከመጠን በላይ በጫነች የጎማ ጀልባ ነበር።
ግለሰቦቹ ከጀልባይቱ ወደ ድንገተኛ አደጋ ደራሽ ሠራተኞች መርከብ የተዘዋወሩ ሲሆን፤ የሕክምና ምርመራ ከተደረገላቸው በኋላ ወደ አንድ የተመረጠ ወደብ ተጓጉዘው እንዲወረዱ የሚደረግ ይህናል።