የሃማስ ታጣቂዎች የእሥራኤልን ሲቪልና ወታደሮች በቁጥጥር ስር ማዋልና መግደል በኋላ የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እሥራኤል ጦርነት ላይ እንደሆነችና በአፀፋውም 'ግዙፍ የበቀል እርምጃ' እንደሚወስዱ አስታወቁ።
ቃላቸውን ተከሎም እሥራኤል በጋዛ ሰርጥ ብርቱ የአየር ጥቃት ፈፅማለች።
ቢያንስ 250 ያህል እሥራኤላውያን ሕይወታቸውን ሲያጡ ከ1100 በላይ ከ20 በበለጡ የእሥራኤል ክፍለ ከተሞች የቀላል መሣሪያዎች ተኩስ ልውውጥ ቆስለዋል።

An Israeli civilian killed by Palestinian militants lies covered in Sderot, Israel, on 7 October 2023. Credit: AP / AP
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ "ለጥቁሩ ቀን ግዙፍ የበቀል እርምጃ እንወስዳለን"
"የምንገኘው ጦርነት ላይ ነው፤ እናሸንፋለንም" ሲሉ፤
የሃማስ መሪ ኢስማኢሊ ሃኒየህ በበኩላቸው ጋዛ ላይ የተጀመረው ወደ ምዕራብ ባንክና ኢየሩሳሌም እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

Palestinian medics inspect a damaged ambulance hit by an Israeli air strike inside Nasser Hospital in Khan Younis, southern Gaza Strip, 7 October 2023. Credit: AP / AP