የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን [[አ-ም-ኮ]] ማናቸውም ዋነኛውን የምርጫ ቀን ሜይ 21 / ግንቦት 13ን ጠብቀው የምርጫ ድምፅ መስጠት የሚሹ ዜጎች በዕለቱ መምረጥ እንደሚችሉና ሌሎች አማራጮችም መኖራቸውን አስታወቀ።
በመላ አገሪቱም 550 ያህል የቅድመ ምርጫ ማዕከላት ተከፍተዋል።
የምርጫ ኮሚሽን ኮቪድ-19 ምርጫውን ሊያስተጓጉል እንደሚችልም ጠቁሞ መራጮች ትዕግስት እንዲያሳዩ አሳስቧል።
በመሆኑም መራጮች የምርጫ ዕቅዳቸውን ቀደም ብለው እንዲያቅዱ አመላክቷል።
በየአካባባኢያቸው ያሉ የምርጫ ጣቢያዎችን ለማወቅ የሚሹ የኮሚሽኑን ድርገፅ aec.gov.au መጎብኘት ይችላሉ።