SBS በ2023 ባካሔደው አዲስ የፕሮግራም ስርጭት ጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከሐሙስ ኦክቶበር 5 / መስከረም 24 አንስቶ SBS Radio 1, SBS Radio 2, SBS Radio 3 እና SBS PopDesiን አካትቶ በመደበኛና ዲጂታል ኦዲዮ የአየር ስርጭት መስመሮች ፕሮግራሞቹን ማስተላለፍ ጀምሯል።
የጊዜ ሰሌዳ ለውጦች
አማርኛ ቋንቋን አካትቶ የተወሰኑ ፕሮግራሞች ወደ SBS ሬዲዮ 3 ተዛውረዋል።
የፕሮግራሞቹን ዝግጅቶች ቀጥታ ስርጭት ቀን ላይ ሲሆን፤ ምሽት ላይ እስካሁን እየተላለፉ ባሉባቸው SBS ሬዲዮ 1 እና SBS ሬዲዮ 2 በድጋሚ መሰራጨታቸውን ሳያቋርጡ ይቀጥላሉ።.
በአዲሱ ስርጭት መሠረት SBS አማርኛ ዘወትር ሰኞ ረቡዕ እኩለ ቀን ላይ በቀጥታ በ SBS ሬዲዮ 3 ይተላለፋል።
የፕሮግራሞቹን የቀን ስርጭቶች በድጋሚ እስካሁን በሚሰራጩባቸው መደበኛ ሰዓቶች የሚተላለፉ ሲሆን፤ የአማርኛ ፕሮግራም ድጋሚ ስርጭትን ሰኞና ዓርብ (ከ10:00-11:00 pm) በ SBS ሬዲዮ 1 ማድመጥ ይችላሉ።
የእኔ ፕሮግራም ስርጭት ላይ መሆኑን እንደምን ማወቅ እችላለሁ?
ቋንቋ | የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም | ድጋሚ |
አማርኛ | SBS ሬዲዮ 3፤ ሰኞ እና ረቡዕ 12:00PM | SBS ሬዲዮ 1፤ ሰኞ እና ዓርብ 10:00PM |
የማድመጫ መንገዶች
እና SBS ኦዲዮ ኧፕ ማድመጥ ይችላሉ። የ SBS Audio Appን ለ iOS በ App Store በኩል ለ Android በ Google Play አማካይነት መጫን ይችላሉ።
እንዲሁም፤ የተመረጡ የ SBS አማርኛ ፖድካስት እና ሬዲዮ ዝግጅቶችን የኧፕል ፖድካስቶች ጨምሮ በ LiSTNR, Spotify እና TuneIn አማካይነት ማድመጥ ይቻልዎታል።
የ SBS Radio 1 ስርጭትን AM ፍሪኩየንሲ ሜልበርን፣ ሲድኒ፣ ካንብራና ኒውካስትል፤ በተጨማሪም በአገር አቀፍ ደረጃ በሌሎች ዋነኛ ከተሞች በመላ አውስትራሊያ በ AM ፍሪኩየንሲ ይተላለፋል።
SBS ሬዲዮ 3 ዲጂታል በመሆኑ፤ አድማጮች DAB+ ዲጂታል በኩል የ SBS ሬዲዮ ጣቢያዎችን ከሲድኒ፣ ካንብራ፣ ሜልበርን፣ አደላይድ፣ ፐርዝ፣ ዳርዊን፣ ሆባርት እና ብሪስበን ማድመጥ ይችላሉ።
በዲጂታል ሬዲዮዎ ለማድመጥ 'SBS Radio' የሚለውን ፈልገው እስኪያገኙ ወደ ፊትና ወደ ኋላ አለዋውጠው በማግኘት ያድምጡ።
አጠቃላዩ የ SBS አዲሱ የስርጭት ፕሮግራም ዕለተ ሐሙስ ኦክቶበር 5 / መስከረም 24 ቢጀምርም የአማርኛ ፕሮግራም አዲሱ የድጋሚ ስርጭት ኦክቶበር 6 / መስከረም 25፤ የቀን ቀጥታ ስርጭት ሰኞ ኦክቶበር 9 / መስከረም 28 እኩለ ቀን ላይ ይሆናል።