የጎንደር ኮማንድ ፖስት የተለያዩ ገደቦችን ጣለ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በቀን 1/8/2015 ተሰብስቦ የሚከተሉትን ክልከላዎች ማስቀመጡን አስታውቋል።

ANRS.jpg

Credit: ANRS

በዚህም መሠረት፦
 1. በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፤
2. በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
3. ከተፈቀደለት የመንግሥት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
 4. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ፣ ገጀራ፣ አንካሴ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
5. በሕግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ፣ የደበቀ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የሕግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በሕግ የተከለከለ ነው።
6. በማንኛውም ቦታና ሰዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
7. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
 8. የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው፦
-የልዩ ኋይል ፣
-የፓሊስ ፣
-የመከላከያ ሠራዊት ፣
-የፌዴራል ፓሊስ መልበስ የተከለከለ ነው።
 9. ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት የተከለከለ ነው።
10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ሥራን ማስተጓጎል በጥብቅ የተከለከለ ነው።
11. የአማራን ሕዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈላችሁ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስታችሁ ወደ ከተማችን የመጣችሁ በከተማችን በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንድትሰባሰቡ እያሳሰብን ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ የተከለከለ ነው
12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ፣ ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በሕግ የሚጠይቅ እንደሚሆን ተገልጿል።


Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service