አውስትራሊያዊው የካቶሊክ ካርዲናል ጆርጅ ፔል በ81 ዓመታቸው በቫቲካን ትናንት ማክሰኞ ጃኑዋሪ 10 ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ካርዲናሉ በሕይወት ሳሉ አወዛጋቢ ወግ አጥባቂ የሃይማኖት መሪ ነበሩ።
ፔል ከ1996 እስከ 2021 የሜልበርን ሊቀጳጳስ የነበሩ ሲሆን፤ ከ2021 እስከ 2024 የሲድኒ ሊቀጳጳስ ሆነው አገልግለዋል።
ከ2014 እስከ 2019 በቫቲካን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የምጣኔ ሃብት ፀሐፊ ሆነው ሠርተዋል።
ሊቀጳጳስ ፔል በ2018 የሜልበርን ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ወቅት በሳቸው የስልጣን ኃላፊነት ስር ባለች ቤተክርስቲያን ትናንሽ ወንዶች ልጆች ላይ ወሲባዊ ጥቃቶች ተፈጽሟል በሚል ታሪካዊ ክስ ተመስርቶባቸው ነበር።
ጉዳዩን የመረመረው ሮያል ኮሚሽን በእሳቸው አስተዳደር ስር በነበረችዋ ቤተክርስቲያን ትናንሽ ወንዶች ልጆች በቄስ ወሲባዊ ጥቃት የተፈማባቸው መሆኑን እያወቁ ተገቢውን እርምጃ አልወሰዱም ሲል የምርመራ ሪፖርት አቅርቧል።
ሆኖም በ2020 በከፍተኛ ፍርድ ቤት ሙሉ ውሳኔ ከክሱ ነፃ ለመሆን በቅተዋል።
የቤት ኪራይ
የአውስትራሊያ የቤት ኪራይ ጭማሪ ከፈጣን ንረቱ በአዝጋሚ ቀጣይ ጭማሮው መቀጠሉን የኮርሎጂክ ዳታ ትንታኔ አመላከተ።
የኮርሎጂክ ዳታ እንዳመለከተው ባለፈው ዓመት የቤት ኪራይ ጭማሮ በአሥር ፐርሰንት ያሻቀበ ሲሆን፤ በዲሴምበር ሩብ ዓመት ላይ ግና መቀዝቀዝን ቢያሳይም በሁለት ጭማሮ አዝግሞ እየተጓዘ መሆኑን ገልጧል።
የፕሮፕትራክ የምጣኔ ሃብት ምርምር ዳይሬክተር ካሜሮን ኩሽነር ለቤት ኪራይ ጭማሮው አዝጋሚ ሁኔታ እንዲቀጥል ያደረገው ምናልባትም ተከራዮች አማራጭ ርካሽ የኪራይ ዘዴዎችን መጠቀም አንዱ አስባብ እንድሚሆን ጠቁመዋል።