በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ የሜልበርን ኩዮንግ ምክር ቤት ወንበራችውን በግል ተወዳዳሪዋ ዶ/ር ሞኒክ ራያን ሊያጡ እንደሚችሉ የሕዝብ አስተያየት ስብስብ እያመለከተ ነው።
በሕዝብ አስተያየቱ መሠረት ሞኒክ ራያን ጆሽ ፍራይደንበርግን 53 ለ 47 እየመሩ ነው።
ዘ አውስትራሊያን ጋዜጣ በዮ ጋቭ ድርጅት በኩል ባሰባሰበው ተጨማሪ የሕዝብ አስተያየት የግል ተወዳዳሪዋ ዞዊ ዳንኤል የሊብራል ፓርቲ ጎልድስታይን ምክር ቤት አባል ቲም ዊልሰንን እየመሩ ይገኛሉ።
የግል ተወዳዳሪዎች የኒው ሳውዝ ዌይልስ ሊብራል ምክር ቤት አባላት ይዘዋቸው ባሉት የምክር ቤት ወንበሮች ማኪላር፣ ዌንትዎርዝና ሰሜን ሲድኒ ብርቱ ፉክክሮችን እያካሔዱ ነው።
በተለያዩ ክፍለ አገራትም እንዲሁ የገጠርና የከተማ ምክር ቤት ወንበሮችን ለመያዝ የግል ተወዳዳሪዎች በተቀናቃኝነት ቀርበዋል።