በአውስትራሊያና ኒውዚላንድ አስተናጋጅነት በሚካሔደው የ2023 ፊፋ የዓለም ዋንጫ ዛሬ ነሐሴ 6 በብሪስበን ላንግ ፓርክ ስታዲየም አውስትራሊያና ፈረንሳይ ባደረጉት የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ የሙሉ መደበኛ 90 ደቂቃና ተጨማሪ 30 ደቂቃ ባዶ ለባዶ ተለያይተዋል።
ግጥሚያው ጥሎ ማለፍ በመሆኑም በፍፁም ቅጣምት እንዲለያዩ በመደረጉ አውስትራሊያ ፈረንሳይን 7 ለ 6 በሆነ እጅግ ልብ ሰቃይ ውጤት በማሸነፍ ለቀጣዩ ግማሽ ፍፃሜ ጥሎ ማለፍ አልፋለች።

France players show dejection after the team's defeat through the penalty shoot-out following the FIFA Women's World Cup Australia & New Zealand 2023 Quarter Final match between Australia and France at Brisbane Stadium on August 12, 2023, in Brisbane / Meaanjin, Australia. Credit: Quinn Rooney/Getty Images
አውስትራሊያ በቀጣዩ የግማሽ ፍፃሜ ጥሎ ማለፍ ግጥሚያ ረቡዕ ነሐሴ 10 የምትጫወተው ዛሬ ምሽት ከሚፋለሙት እንግሊዝና ኮሎምቢያ አሸናፊ ጋር ይሆናል።
ቀደም ሲል ኔዘርላንድስን 2 ለ 1 የረታችው ስፔይንና ጃፓንን በተመሳሳይ ውጤት ጃፓንን 2 ለ 1 ድል የነሳችው ስዊድን ማክሰኞ ነሐሴ 9 አመሻሽ ላይ ለፍፃሜ ዋንጫ ለመቅረብ ብርቱ ፉክክር ያካሂዳሉ።