አውስትራሊያ ከዓለም በከፍተኛ ደረጃ የሜላኖማ መጠን የተስፋፋባት በመሆኗ መጠነ ሰፊ የግ ን ዛቤ ማስጨበጫ ቅስቀሳ እንዲካሔድ በፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ ተጠየቀ።
በአውስትራሊያ ሜላኖማ ተቋም ገለጣ መሠረት አውስትራሊያ ውስጥ የሜላኖማ ካንሰር ጥቃት በአብዛኛው ጎልቶ የሚከሰተው ዕድሜያቸው ከ20 እስከ 39 ባሉት ላይ ነው።
አውስትራሊያ ውስጥ በየ30 ደቂቃው አንድ አውስትራሊያዊ/ት የሜላኖማ ጥቃት የሚያገኘው/ኛት ሲሆን፤ በየስድስት ሰዓታቱ በሜላኖማ ሳቢያ የአንድ ሰው ሕይወት ያልፋል።
ይህንኑ ተመርኩዞም ገላን ለፀሐይ በማጋለጥ ቆዳን ማጠየምንና የተለያዩ ቆዳ ማጠየሚያ ምርቶችን አስመልክቶ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እንዲሰጥ መንግሥት ሰፊ ተሳትፎ እንዲያደርግ 7,500 ፊርማዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተሰባስቧል።
የጤናና አረጋውያን ክብካቤ ዲፓርትመንት ለSBS News እንደገለጠው መንግሥት ከአውስትራሊያ ካንሰር ምክር ቤት ጋር በመተባበር ለብሔራዊ የቆዳ ካንሰር ቅድመ መከላከል ዘመቻ $10 ሚሊየን ማዋሉን ገልጧል።
የቅስቀሳ ዘመቻውም ሁሉንም አውስትራሊያውያን በተለይም ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም አስታውቋል።
የማኅበራዊ ሚዲያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ማስታወቂያውም በዩቲዩብ፣ ፌስቡክና ኢንስታግራም መሰራጨቱን አመላክቷል።
ኪርናን ፎርብስ (A-K-A)
ዝነኛው የደቡብ አፍሪካ ራፐር ኪርናን ፎርብስ ወይም A-K-A በመባል የሚታውቀው ድምፃዊ ከአንድ የደርባን ምግብ ቤት በራፍ ላይ ተገድሏል።
የ 35 ዓመቱ ድምፃዊ በርካታ የደቡብ አፍሪካ ሽልማቶችን ተሸልሟል፤ ለበርካታ ጊዜያትም ለዩናይትድ ስቴትሱ የጥቁር የመዝናኛ ቴሌቪዥን (BET) እንዲሁም አንዴ ለሙዚቃ ቴሌቪዥን (M-T-V) በዕጩ ተሸላሚነት ቀርቧል።

AKA during the Comedy Central Roast of AKA held at Montecasino's Teatro, Fourways, on February 21, 2019, in Johannesburg, South Africa. Credit: Gallo Images / Oupa Bopape
ሟቾቹ በሁለት ታጣቂ ግለሰቦች ከቅርብ ርቀት በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ባለፈበት ወቅት ወደ ምሽት ክለብ እያመሩ እንደነበር ተገልጧል።
በፖሊስ በኩል ምርመራ እየተካሔደ ሲሆን፤ የግድያው መንስኤ ምን አንደሆነ እስካሁን ይፋ አላደረገም።
የድምፃዊውን ሕልፈተ ሕይወት አስመልክቶ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጥልቅ ሐዘኑን ገልጧል።