በድምፃዊ ዳንኤል ኢስትሪን የመድረክ መሪነት የሚመራው የፐርዝ - አውስትራሊያ ቮያጀር ባንድ በ67ኛው ዩሮ ቪዢን የዘፈን ውድድር ለፍፃሜ አልፏል።
ከጀርመን ወደ አውስትራሊያ ፈልሶ የመጣው ዳኒኤልና ቮያጀር ባንድ እሑድ ሜይ 14 በምሥራቅ አውስትራሊያ ሰዓት አቆጣጠር 5:00 am ለሚካሔደው የፍፃሜ ውድድር ያለፉት ከ16 አገራት ጋር ተወዳድረው ለፍፃሜ ከሚቀርቡት 10 ተፎካካሪዎች አንዱ በመሆን ነው።
ለመጨረሻ ማጣሪያ ለአሸናፊነት የበቁት "Promise - ቃል ኪዳን" በሚለው ዘፈን ነው።
በጀት 2023/24
የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን መሪ ፒተር ዳተን ሜይ 9 በበጅሮንድ ጂም ቻልመርስ የቀረበው የፌዴራል መንግሥቱ በጀት ለዋጋ ግሽበት ዳራጊ እንደሆነና መካከለኛ ገቢ ላላቸው አዋኪ እንደሆነ በማመላከት ትችት ሰነዘሩ።
አቶ ዳተን ወጪዎቻቸውን ለመሸፈን በሚሊየን የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን በኑሮ ትግል ላይ እንዳሉ በመጥቀስም ጭንቀታቸውን የሚገታ አስቸኳይ እገዛ እንደሚያሻ ተናግረዋል።