ጽሕፈቱ በማሕበራዊ ትስስር ገፁ እንዳሰፈረው ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ስታስጀምር፣ በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢልየን ችግኞችን ለመትከል ማቀዷ ይታወሳ ብሏል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ ኢትዮጵያ ከታቀደው ግብ አልፋ በመላ ሀገሪቱ 25 ቢልየን ችግኞች በመትከል የአራት ዓመት ዕቅዷን አሳክታለች ሲልም አክሏል።
በዚህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለደን መልሶ ልማት ላደረገችው አስተዋጽዖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝታለች ብሏል።