በዘንድሮው 2023 / 2015 ሉላዊ የወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ ምደባ ከ145 የዓለም አገራት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሩስያ፣ ቻይና፣ሕንድ፣ እንግሊዝ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ፓኪስታን፣ ጃፓን ፈረንሳይና ጣሊያን በቅደም ተከል ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
አውስትራሊያ ከዓለም 16ኛ ሥፍራን ስትይዝ ከ145ቱ አገራት የመጨረሻው የኃይል ሰእንጠረዥ ላይ የሠፈረችው የደቡብ እስያይቷ ብሁታን ናት።
ከአፍሪካ በወታደራዊ ኃይል ጥንካሬያቸው ግብፅ፣ አልጀሪያ፣ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ አንጎላ፣ ሞሮኮ፣ ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ፣ አንጎላና ሱዳን በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ አሥረኛ ተመድበዋል።
ከ38ቱ የአፍሪካ አገራት በወታደራዊ ጥንካሬዋ የመጨረሻው ሠንጠረዥ ላይ ያረፈችው ቢኒን ናት።
በመካከለኛው ምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ የወታደራዊ ኃይል ምደባ ዘርፍ ቱርክ፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ እሥራኤል፣ ሳኡዲ አረቢያ፣ አልጄሪያ፣ ኢራቅ፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬት ፣ ሞሮኮና ሶሪያ ከአንደኛ እስከ አሥረኛ የቅደም ተከተል ሥፍራ ይዘዋል።
ከ20 የመካከለኛውና ሰሜን አፍሪካ አገራት የመጨረሻው እርከን ላይ የተመደበችው ሊባኖስ ናት።
የወታደራዊ ኃይል ጥንካሬ ደረጃ ምደባው የተካሔደው በግሎባል ፋየርፓወር አማካይነት ሲሆን፤ የደረጃ ምደባ አንኳር መመዘኛውን ያደረገውም የአገራቱን የወታደራዊ ክፍሎች ጥንካሬ፣ የፋይናንስ ቁመናና የወታደራዊ ቁሳቁሶች ብቃትና ጂኦግራፊን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
የወታደራዊ ልዕለ ኃይል የላቀ ሠንጠረዥ ደረጃ 0.0000 ሲሆን አንዳቸውም የዓለም አገራት ከዚያ ደረጃ ላይ አልደረሱም።
የዓለም ገናናዎቹ አገራት የወታደራዊ ልዕለ ኃይል የላቀ ሠንጠረዥ ደረጃ መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ 0.0712፣ ሩስያ 0.0714 ቻይና 0.0722 ሲሆን ከአፍሪካ ግብፅ 0.0224 ኢትዮጵያ 0.07979 ላይ ይገኛል።