በኢትዮጵያና የሕወሓት ገዲብ ወታደራዊ አመራሮች መካከል የስምምነት ፊርማ ናይሮቢ ላይ ተካሔደ

የከባድ መሣሪያዎች ትጥቅ ፍቺ በሚካሔድበት ወቅት የውጪና የመከላከያ ሠራዊ አካላት ያልሆኑ ኃይሎች ክልሉን ይለቅቃሉ

Peace Diplomacy.jpg

Chief of staff of the Ethiopian Armed Forces and Field Marshal Berhanu Jula (L) shakes hands with Commander-in-chief of the Tigray rebel forces General Tadesse Worede (R) as, former Nigeria's President Olusegun Obasanjo (CL) and former Kenya's President Uhuru Kenyatta (CR) applaud during the signing ceremony of the declaration of the senior commanders meeting on the implementation of the Ethiopia permanent cessation of hostilities agreement between the government of Ethiopia and the Tigray People's Liberation Front (TPLF) in Nairobi on November 12, 2022. Credit: YASUYOSHI CHIBA/AFP via Getty Images

የፕሪቶሪያውን የጥቅምት 23 በቋሚነት ከግጭት መገታት የሰላም ስምምነት መርህ ተከትሎ በኢትዮጵያ መንግሥት የመከላከያና የሕወሓት ታጣቂዎች ገዲብ ወታደራዊ አመራር አባላት መካከል ቅዳሜ ሕዳር 3 ቀን 2015 በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል።

ኢትዮጵያ አንድ የመከላከያ ሠራት ብቻ እንደሚኖራት ከአመኔታ ላይ የተደረሰበትን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተመርኩዘው ለአራት ቀናት የመከሩትና የውል ስምምነቱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት በኢፌዲሪ መከላከያ በኩል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊል ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ሲሆኑ፤ በሕወሓት በኩል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ናቸው።

በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ወገኖች፤
  • ማናቸውንም ዓይነት ወታደራዊ ግጭቶች መግታትና መታቀብ
  • ከሕዳር 6 አንስቶ አዛዦች በጦሮቻቸው ዘንድ ተገኝተው የትጥቅ ፍቺ ሂደቱን አስመልክተው ማብራሪያዎችን መስጠት
  • ከሰባት ቀናት ማብራሪያ በኋላ ባሉት አራት ቀናት የፌዴራል ባለስልጣናት በሕገ መንግሥቱ መሠረት የአገልግሎቶች ቅጠላን አካትቶ አካትቶ በሁሉም አካባቢዎች ላይ ኃላፊነትን ይወስዳሉ
  • የከባድ መሣሪያዎች ትጥቅ ፍቺ በሚካሔድበት ወቅት የውጪና የመከላክያ ሠራዊ አካላት ያልሆኑ ኃይሎች ክልሉን ይለቅቃሉ
  • ስምምነቱ ከተፈረመበት ቀን አንስቶ ለቀላል መሣሪያዎች ፍቺ ትግበራ ጥምር አስፈፃሚ ኮሚቴ በሁለቱ ወገኖች አዛዦች አማካይነት በማቆም ግልፅ የአፈፃፀም ጊዜን የሚያመልክት ዕቅድ ሪፖርት እንዲቀርብ ያስደርጋሉ
  • ጥምር ኮሚቴው ከእያንዳንዱ ወገን ሁለት - ሁለት ተወካዮች ይኖረዋል፤ በአፍሪካ ኅብረት በኩል አንድ ተቆጣጣሪና አረጋጋጭ ቡድን ይሰየምለታል
  • የአፍሪካ ኅብረት ተቆጣጣሪና አረጋጋጭ ቡድን ስምምነቱ ከተፈረመበት 10ኛ ቀን አንስቶ ሥራውን ይጀምራል
  • ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃቶችን ማድረስ የተከለከለ ይሆናል፣ ለሲቪል ተቋማትና መሠረተ ልማት አውታሮች ጥበቃ ይካሔዳል
  • እርዳታ ለሚሹ ሁሉ ገደብ ያልተጣለበት ሰብዓዊ ረድኤት ወደ ትግራይ አጎራባች ክፍለ አገራት እንዲዘልቅ ይደረጋል
  • የግብረ ሰናይ ድርጅት ሠራተኞች ገደብ ያልተጣለበት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ማስቻልን ግድ ይላል
  • የግብረ ሰናይ ድርጅቶችና ሠራተኞቻቸው የደኅንነት ዋስትና እንዲያገኙ ያደርጋል
  • ስምምነቱ ከዳር እንዲደርስ ሁለቱ ወገኖች በሚቆጣጠሯቸው የሚዲያ መድረኮች በኩል ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ፈቃዳቸው ሆኗል።
አራት ቀናት የፈጀውንና ከውል ስምምነት ላይ የደረሰውን የሁለቱ ወገኖች ጥረት አስመልክቶ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ተወካዮች የሆኑት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ኦባሳንጆና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚደንት ኬንያታ ምስጋናና አድናቆታቸውን ቸረዋል።
Peace agreement.jpg
Commander-in-chief of the Tigray rebel forces General Tadesse Worede (2ndL) Chief of staff of the Ethiopian Armed Forces and Field Marshal Berhanu Jula (3rdL), former Nigeria's President Olusegun Obasanjo (5thL) and former Kenya's President Uhuru Kenyatta (R) sign documents during the signing ceremony of the declaration of the senior commanders meeting on the implementation of the Ethiopia permanent cessation of hostilities agreement between the government of Ethiopia and the Tigray People's Liberation Front (TPLF) in Nairobi on November 12, 2022 Credit: YASUYOSHI CHIBA/AFP via Getty Images
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በበኩሉ ኢጋድ፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ ዩናይትድ ስቴትስንና የአፍሪካ ልማት ባንክን በስምምነት ሂደቱ ላይ ስላበረከቱት ድጋፎች አድናቆቱን ገልጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም፤ የኢፌዲሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት "በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በታቀደለት መንገድ እንዲሄድ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት እየሠራ ነው" ሲል ሕዳር 3 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የኮሙኒኬሽን አገልግሎቱ አክሎም "ከዚሁ ጎን ለጎን በሰላም ስምምነቱ መሠረት የሕወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ አዛዥና የሕወሓት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢ መክረዋል"

"በሰላም ስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበትንና መከላከያ ወደ መቀሌ የሚገባበት ዕቅድ ላይም ተስማምተዋል" ሲል በመግለጫው ላይ አስፍሯል።

Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service