አርጀንቲና ዛሬ ማለዳ ክሮኤሽያን 3 ለ 0 ረትታ ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ግጥሚያ በቅታለች።
ግቦቹን ለአርጀንቲና ያስቆጠሩት ሊዮኔል ሚሲ በ34ኛዋ ደቂቃ የመጀመሪያዋን ግብ (በፍፁም ቅጣት ምት)፣ ሁሊያን አልቫሬዝ በ39ኛ እና 69ኛ ደቂቃዎች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ግቦችን ከመረብ አኑሯል።

Lionel Messi of Argentina celebrates with Julian Alvarez (L) of Argentina his team's second goal during the FIFA World Cup Qatar 2022 semi final match between Argentina and Croatia at Lusail Stadium on December 13, 2022 in Lusail City, Qatar. Credit: Markus Gilliar - GES Sportfoto/Getty Images
የክሮኤሽያ ቡድን በመከላከል ላይ ያደላ ሲሆን፤ ለግብ አስጊ የነበረ ሙከራውን ከአንድ ጊዜ በላይ አላስቆጠረም።
ሽንፈቱ እንደ ደጋፊዎቹ ሁሉ ተስፈኛ የነበሩትን የተጫዋቾቹንም ልብ ሰብሯል።

Luka Modric of Croatia looks dejected during the FIFA World Cup Qatar 2022 semi final match between Argentina and Croatia at Lusail Stadium on December 13, 2022 in Lusail City, Qatar. Credit: Marc Atkins/Getty Images
ፈረንሳይ እና ሞሮኮ (ሐሙስ ዲሴምበር 15 / ታሕሳስ 6) 6:00 am [AEDT]