ስዊድን በዘንድሮው የዩሮ ቪዥን የዘፈን ውድድር የመጀመሪያውን ሥፍራ በመያዝ ለአሸናፊነት ስትበቃ፤ የአውስትራሊያ ቮያጀር ባንድ የዘጠነኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቋል።
ስዊዲናዊቷ ሎረን "ታቱ" በሚለው ዘፈንዋ በማሸነፍ ፊንላንድን ለሁለተኛ ደረጃ ዳርጋለች።
ፊንላንድ ሁለተኛ ደረጃን የያዘችው በ "ቻቻ" 526 ነጥቦችን በማግኘት ሲሆን፤ ስዊድን የውድድሩ አሸናፊ የሆነችው 583 ነጥቦችን በማስመዝገብ ነው።
የስዊድኗ ሎረን የዩሮ ቪዥን 2023 የዘፈን ውድድርን ለሁለተኛ ጊዜ በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ሴት ዘፋኝ ለመሆን በቅታለች። የመጀመሪያ ድሏን ያጣጣመችው በ2012 "ዩፎሪያ" ዘፈኗ ነው።
የአውስትራሊያው የፐርዝ ቮያጀር ባንድ አባላት በዘንድሮው 67ኛው የዩሮ ቪዥን ውድድር "ፕሮሚስ" በሚለው ዘፈናቸው የ37 አገራትን የድጋፍ ድምፆች በማግኘት በዘጠነኛነት ለማጠናቀቅ በቅተዋል።

Australia's Voyager performed in the grand final of the Eurovision Song Contest 2023, where they placed ninth. Credit: AAP / Aaron Chown/PA/Alamy

Australia's Eurovision results over the years have been strong but have not amounted to a winner. Credit: SBS