Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ 35 ፕሬዝዳንቶችና 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች ይሳተፋሉ

ቀጣዩን የአፍሪካ ኅብረት ፕሬዝዳንትነት ኮሞሮስ ከሴኔጋል ትረከባለች።

Amb Alem.jpg

Ambassador Meles Alem, Spokesperson of the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia. Credit: MFAE

በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ላይ የ51 አገራት ልዑካን ቡድኖች እንደሚሳተፉ ታዉቋል፡፡

በመድረኩ ላይ 35 ርዕሰ-ብሔሮች፣ አራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ 11 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ 13 ቀዳማዊ እመቤቶችና 10 የዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎች ይታዳማሉ ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ከነገ ጀምሮ 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ መካሄድ ይጀምራል፡፡

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ጉባኤው የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ጉዳይ ላይ በስፋት እንደሚመክር ተናግረዋል።

በጉባኤው የፀጥታ ምክር ቤት ማሻሻያ እና የተለያዩ የሕግ ሰነዶች ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ቀጣዩን የአፍሪካ ኅብረት ፕሬዝዳንትነት ኮሞሮስ ከሴኔጋል ትረከባለች ብለዋል።


1 min read

Published

By Stringer Report

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now