የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያይተዋል
በውይይታቸው ወቅት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ብሊንከን በቀጣይ ከሰብዓዊ ድርጅቶች እና ከከሲቪክ ተቋማት ጋር በሰብዓዊ ዕርዳታ ስርጭት፣ በምግብ ዋስትና እና በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ እንደሚነጋገሩ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በተጨማሪም ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ጋር እንደሚገናኙ ተነግሯል።
አቶ ብሊንከን ወደ ኢትዮጵያና ኒጀር ከማቅናታቸው በፊት የአፍሪካ አገራት በምህብ ዋስትና፣ የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ፣ ሉላዊ ጤና፣ ሰብዓዊ መብቶችና ሰላም ሁነኛ ሽርካዎች መሆናቸውን አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የዩናይትድ ስቴትስ አቻቸውን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ገልጧል።