የሌበር ፓርቲ በቅዳሜው አገራዊ ምርጫ ለመንግሥትነት ከበቃ $970 ሚሊየን ዶላርስ ለሜዲኬይርና የአካባቢ ጤና መደጎሚያ እንደሚያውል አስታወቀ።
ከበጀቱ ውስጥ $750 ሚሊየን ለሜዲኬይር ግብረ ኃይል ማጠናከሪያ፣ ሕመምተኞች ሐኪሞች ዘንድ የተሻለ ተደራሽነት እንዲኖራቸው፣ ሆስፒታሎች ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ፣ ውስብስብና ስር የሰደዱ ሕመሞችን በተሻለ ሁኔታ ለማከም የሚውል ይሆናል።
የመኖሪያ ቤት ፖሊሲ
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ዛሬ ብሪስበን ላይ በይፋ በሚከፈተው የሊብራል ፓርቲ አገር አቀፍ ምርጫ መክፈቻ ላይ የቤት ፖሊሲያቸውን ያስታውቃሉ።
በአዲሱ ፖሊሲ መሠረት 1.3 ሚሊየን ያህል ዕድሜያቸው ከ55 በላይ የሆኑ ሰፋፊ ቤቶቻቸውን ሸጠው ወደ አነስተኛ ቤት በመቀየር እስከ $300,000 በግለሰብ ደረጃ ወደ ጡረታ አበላቸው መጨመር ይችላሉ።
ይህም ወጣት ቤተሰቦች ሰፋፊ ቤቶችን ለመግዛት እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑ ተጠቅሷል።