'ቪዛ በሶስት ቀናት ውስጥ' ወደ አውስትራሊያ መምጣት ለሚፈልጉ አስተማሪዎችና ነርሶች አፋጣኝ ቪዛ ሊሰጥ ነው

የአውስትራሊያ መንግሥት የቪዛ ቅደም ተከተሎቹ ላይ ያካሔደውን የማሻሻያ ለውጥ ተከትሎ ወደ አውስትራሊያ መጥተው መሥራት ለሚሹ አስተማሪዎችና የጤና ክብካቤ ሠራተኞች የቪዛ ማመልከቻ ሂደት በሶስት ቀናት ውስጥ የሚከወን ይሆናል።

Visa applications for nurses.jpg

Visa applications for nurses are now only taking three days to process. Credit: Getty / JohnnyGreig

የአውስትራሊያ የአገር ውስጥ ጉዳዮች ዲፓርትመንት ቀደም ሲል የነበረውን የፍልሰተኛ ባለ ሙያ የሥራ ዝርዝር ቅደም ተከተል እርከን አሰጣጥ ከወቅቱ የሠራተኞች እጥረት አኳያ አብሮ የሚሔድ አይደለም በሚል ዕሳቤ እንዲሻር ወስኗል።

ቀደም ሲል የነበረው አሠራር 44 የሙያ ዘርፎችን የፍልሰተኛ ባለ ሙያ የሥራ ዝርዝር ውስጥ አስፍሮ ግብር ላይ መዋል የጀመረው ሴፕቴምበር 2020 ሲሆን፤ ከዚህ ዓመት 2022 ኦክቶበር 28 አንስቶ አሠራሩ እንዲገታ ተደርጓል።

የሙያ ዝርዝሩ ውስጥ ተካትተው የነበሩት መሐንዲሶች፣ ዋና ምግብ አብሳይ (ሼፍ)፣ የሂሳብ ባለሙያ፣ የሥነ አዕምሮ ሐኪም፣ ፕሮግራም ነዳፊዎች እና ፋርማሲስቶች የሚገኙበትና አስተማሪዎች የተገለሉበት ነበር።

በአዲሱ ሚኒስትራዊ መምሪያ ቁጥር 100 አሠራር ግና የቅድሚያ ቪዛዎች የጤናና የትምህርት መስኮችን እንዲያካትት ተደርጓል።
Visa applications.jpg
Visa applications for nurses are now only taking three days to process. Credit: Getty / The Good Brigade
የአዲሱን አሠራር ለውጥ አስመልክቶ "ማመልከቻዎቹ እየተገመገሙ ያሉት በሶስት ቀናት ውስጥ ነው" ሲሉ ለSBS መግለጫ የሰጡት የዲፓርትመንቱ ቃል አቀባይ ገልጠዋል።

በዚህም መሠረት የትምህርት ቤት መምህራን፣ የጤናና የረድኤት ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች፣ የሕፃናት ክብካቤ ማዕከል ሥራ አስኪያጆች፣ የሕክምና ሳይቲስቶች፣ የምክር አገልግሎት ሰጪዎች፣ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች፣ የማኅበራዊ ጉዳይ ሠራተኞችና ለሕክምና ቴክኒሺያኖች ማመልከቻዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ ይገኛል።

አዲስ የሙያ ቪዛ ማመልከቻዎች ቅደም ተከተል

በአዲሱ ሚኒስትራዊ መምሪያ የሙያ ቪዛ ማመልከቻዎች እንደሚከተለው ቅደም ተከተል እንዲይዙ ተደርጓል።

1. የጤና ክብካቤ ወይም የአስተማሪነት ሙያ ማመልከቻዎች


2. የአሠሪ ስፖንሰር ቪዛዎች፣ ከዕውቅና ደረጃ ጋር ይሁንታ ባለው ስፖንሰር የታጩ አመልካቾች


3. ተመርጦ ለተሰየመ ሪጂናል አካባቢ


4. ለቋሚና ጊዜያዊ ቪዛ ንዑስ መደቦች፣ የቪዛ ማመልከቻዎቹ በፍልሰት ፕሮግራም ታሳቢ የሚሆኑ፣ ንዑስ መደብ 188 (የንግድ ፈጠራና ሙዋዕለ ንዋይ (ጊዛዊ) ቪዛን ሳያካትት


5. የተቀሩ ቪዛ ማመልከቻዎች በሙሉ።

ከላይ ያሉት ዘርፎች ቅድሚያ የሚሰጠው መመዘኛን ለሚያሟሉ የፖስፖርት ባለቤቶች ይሆናል። ሁሉም የቪዛ ምንጮች ለሁሉም አገር ዜጋ ክፍት አይደሉም።

በእያንዳንዱ ዘርፍ ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ከአውስትራሊያ ውጪ ላሉ ጊዜያዊና ቋሚ ማመልከቻዎች ነው። የፌዴራል መንግሥቱ በገባው ቃል መሠረት የፍልሰት ቪዛ ሙያ ዝርዝሮች ይበልጡን ስሉጥ እንዲሆኑ ተጨማሪ ክለሳዎችን በማድረግ የማሻሻያ ለውጦችን ሊያካሂድ ይችላል።

ይህንኑ አስመልክቶ በፌብሪዋሪ መጨረሻ ቀዳሚ፤ በማርች/ኤፕሪል ላይ የኤክስፐርቶች ማጠቃለያ ስትራቴጂ ሪፖርት ይቀርባል።
Anthony Albanese's government has made changes to Australia's skilled migration program.jpg
Anthony Albanese's government has made changes to Australia's skilled migration program since winning the election in May. Credit: AAP / Lucas Coch
The new criteria applies to these skilled visas:

  • Subclass 124 (Distinguished Talent)
  • Subclass 186 (Employer Nomination Scheme)
  • Subclass 187 (Regional Sponsored Migration Scheme)
  • Subclass 188 (Business Innovation and Investment) (Provisional)
  • Subclass 189 (Skilled - Independent)
  • Subclass 190 (Skilled - Nominated)
  • Subclass 191 (Permanent Residence (Skilled Regional))
  • Subclass 457 (Temporary Work (Skilled))
  • Subclass 482 (Temporary Skill Shortage)
  • Subclass 489 (Skilled - Regional (Provisional))
  • Subclass 491 (Skilled Work Regional (Provisional))
  • Subclass 494 (Employer Sponsored Regional (Provisional))
  • Subclass 858 (Global Talent)
  • Subclass 887 (Skilled - Regional)
  • Subclass 888 (Business Innovation and Investment (Permanent).
በአሁኑ ወቅት ክፍት ሆኖ ያለው ጊዜያዊ የፍልሰት ሙያ ቪዛ ለሠራተኞች በዓመት $53,900 ያህል ገቢ የሚያስገኝ ነው።

እንደ Seek የሠራተኞች ኦንላይን ገበያ ምልከታ መምህራን በአማካይ ከ85,000 እስከ $100,000 በዓመት ሲያገኙ፤ ነርሶች ከ $70,000 እስከ $90,000 ድረስ ተከፋይ ናቸው።

ውዝፍ የቪዛ ማመልከቻዎች ቅነሳ

ከጁን 1 አንስቶ የአገር ውስጥ ጉዳዮች ዲፓርትመንት ከ43,000 በላይ ለሆኑ ጊዜያዊና ለ47,000 ቋሚ የቪዛ ማመልከቻዎች ውሳኔውን ቸሯል።

የኢሚግሬሽን ሚኒስትር አንድሩ ጂለስ ባለፈው ኖቬምበር እንደተናገሩት ከ100 ሚሊየን በላይ ውዝፍ ሆነው ተቀምጠው የነበሩት ማመለከቻዎችን ወደ 755,000 ዝቅ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል።

ይህንኑ ተግባር ለመከወን ከሜይ ወር ጀምሮ ጊዜያዊና የፍልሰት ቪዛ ማመለከቻዎችን ለመከወን 442 ተጨማሪ ሠራተኞች ተመድበው እየሠሩ መሆኑን SBS ተገንዝቧል።

ካለፈው የፋይናንስ ዓመት ጋር በተመሳሳይ መልኩ ሲነፀፀር በ2022-23 ጊዜያዊ የሙያ ቪዛዎች ይሁንታ በ120 ፐርሰንት ከፍ ብሏል።

Share

Published

Updated

By NACA, Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service