Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት ቁጥር ወደ 3.7 ፐርሰንት አሻቀበ

የነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ ደጋፊዎች ዓላማና ተልዕኳቸውን አስመልክቶ አውስትራሊያውያንን ግንዛቤ ለማስጨበጥ የድርጊት መርሐ ግብራቸውን በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሊጀምሩ ነው።

A general view of a Centrelink office in Footscray.jpg

A general view of a Centrelink office in Footscray on March 29, 2021, in Melbourne, Australia. Credit: Darrian Traynor/Getty Images

የአውስትራሊያ ሥራ አጥነት ቁጥር ከ 3.5 ፐርሰንት ወደ 3.7 ፐርሰንት ከፍ አለ።

የአውስትራሊያ ስታቲስቲክ ቢሮ እንዳመለከተው የሥራ ተሳትፎ ከ 66.5 ፐርሰንት በ 0.1 ፐርሰንት ዝቅ ብሏል።

 በሪፖርቱ መሠረት 11,500 ሥራዎች ታጥፈዋል፤ አንድ የአውስትራሊያ ዶላር ከ69 የአሜሪካ ሳንቲም በታች ወርዷል።

ባለፈው ወርኃ ዲሴምበር የሥራ አጥነት ቁጥር 3.5 ፐርሰንት የነበረ ሲሆን፤ 14,600 ሥራዎች ታጥፈዋል።

 ድምፅ ለፓርላማ

የነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ ብሔራዊ ፕሮግራም በዚህ ዓመት ሊካሔድ ስለተወጠነው ሕዝበ ውሳኔ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስና ግንዛቤዎችን ለማስጨበጥ ደጋፊ አባላቱ በዚህ ሳምንት መጨረሻ የድርጊት መርሐ ግብራቸውን በይፋ ሊዘረጉ ነው።

የኡሉሩ መግለጫ አቀናባሪዎች በብሔራዊ የድርጊት ሳምንት ውስጥ ቅዳሜ ፌብሪዋሪ 18 በኦንላይና በአካል ተገናኝተው የመረጃ ልውውጥ ውይይቶችን ለማካሔድ ተልመዋል።

የኡሉሩ ውይይት ተባባሪ ሊቀመንበር ፓት አንደርሰን አውስትራሊያውያን በዚህ ዓመት በሚከናወነው ሕዝበ ውሳኔ ስለ ነባር ዜጎች ድምፅ ለፓርላማ ተልዕኮን በውል ተገንዘበው ድምፃቸውን እንዲሰጡ የሚሹ መሆኑን አመልክተዋል።


1 min read

Published

By NACA, Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now