የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በባጃጅ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የጣለውን ዕገዳ እንዲያነሳና መፍትሔ እንዲያበጅ ኢሰመኮ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎትን ከየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አካባቢ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይሰጥ እገዳ መጣሉና እገዳውም ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ እስከሆነበት ጊዜ አለመነሳቱ በተለያዩ ሰብአዊ መብቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ገደብ የሚጥል እርምጃ በመሆኑ እጅግ አሳሳቢነቱን አስታወቀ።

Three-wheelers.jpg

Three-wheelers. Credit: Buddhika Weerasinghe/Bloomberg via Getty Images

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ እገዳውን አስመልክቶ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ “የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት እንዲያስችል የአሠራር ማሻሻያ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑንና፣ የማሻሻያ ሥራው ተሠርቶ እስኪጠናቀቅ እና የባጃጅ ትራንስፖርት የአገልግሎት አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪሰጥበት ድረስ” በሚል ምክንያት ከየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ እገዳ መሆኑን ማሳወቁ ይታወሳል። 

ኮሚሽኑ ይህንን እገዳ ተከትሎ የደረሱትን አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችን አነጋግሯል። ኃላፊዎቹ በከተማዋ ወደ 10 ሺህ የሚገመቱ “የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ፈቃድ ያልተሰጣቸው መሆኑን፣ እንደ አንድ አገልግሎት ሰጪ በከተማዋ አሠራር ሥርዓት ያልተዘረጋላቸው መሆኑን፣ እንዲሁም ሌሎችም ተዛማጅ ችግሮች” መኖራቸውን ይገልጻሉ። 

በተጨማሪም “ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ከዋና መንገዶች ውጪ ባሉ ውስጥ ለውስጥ መንገዶች እስከ ሁለት ኪሎ ሜትር ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ማስተካከያ እየተወሰደ መቆየቱን”፤ ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች ባጃጆቹ ከተቀመጠላቸው የእንቅስቃሴ አካባቢ ውጪ በዋና መንገዶች ላይ ሲሠሩ መታየታቸው እና የከተማው የትራንስፖርት ፍሰት ላይ ጫና መፍጠሩን ይናገራሉ። 

እገዳው በሁሉም ቦታ የተደረገው “ልዩነት እና መድሎ ላለመፍጠር” እንደሆነና የባጃጅ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች በማኅበር ተደራጅተው የሚሠሩ በመሆኑ አሠራሩን ስለማሻሻል ከማኅበራቱ ጋር የተደረጉ ውይይቶች እንደነበሩ ያስረዳሉ።

በሌላ በኩል እገዳው በተጣለበት በየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. “በተቃውሞ መንገድ የዘጉ የጋርመንት አካባቢ ባጃጅ ሹፌሮች” ታስረው የነበረና ወደ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስትና መለቀቃቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡ ኮሚሽኑ ባደረገው

ክትትል እገዳው በከተማዋ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ መሆኑ የባጃጅ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎቹንና ቤተሰቦቻቸውን ብቻ ሳይሆን፣ እጅግ በርካታ ተጠቃሚዎችንም ችግር ላይ እንደጣለ መረዳት ተችሏል።

መንግሥት ሰዎች ሥራቸውን እና የመረጡትን መተዳደሪያ ያለአግባብ እንዳያጡ ማድረግን ጨምሮ የመረጡትን እና የተቀበሉትን ሥራ እንዲሠሩ የማስቻል ኃላፊነት አለበት።

በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 41(1) መሠረት “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሀገሪቱ ውስጥ በማንኛውም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የመሰማራት እና ለመተዳደሪያው የመረጠውን ሥራ የመሥራት መብት” ያለው ሲሆን በንዑስ-አንቀጽ 2 እንደተመለከተው መተዳደሪያውን፣ ሥራውን እና ሙያውን የመምረጥ መብት አለው።

ይህ መተዳደሪያን የመምረጥ/በመረጡት ሥራ የመሰማራት መብት (the right to choose one’s livelihood/work) ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነዶችም የተረጋገጠ መብት ነው፡፡

በተጨማሪም የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 41(6) እንደሚደነግገው መንግሥት ለሥራ አጦች እና ለችግረኞች ሥራ ለመፍጠር የሚያስችል ፖሊሲ የመከተል፤ በሚያካሂደው የሥራ ዘርፍ ውስጥ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሥራ ፕሮግራሞችን የማውጣት እና ፕሮጀክቶችን የመቅረጽ ግዴታ አለበት።

የዚሁ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ 7 ደግሞ መንግሥት ዜጎች ጠቃሚ ሥራ የማግኘት ዕድላቸው እየሰፋ እንዲሄድ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት ይደነግጋል።

ሕገ-መንግሥቱ በምዕራፍ አስር ከተካተቱት የብሔራዊ ፖሊሲ መርሆችና ዓላማዎች መካከል ስለኢኮኖሚ ነክ ዓላማዎች በሚደነግገው በአንቀጽ 89(2) ላይ መንግሥት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ለማድረግ ሁኔታዎች የማመቻቸት ግዴታ እንዳለበት ይገልጻል።

የዚሁ አንቀጽ ንዑስ-አንቀጽ 8 ደግሞ መንግሥት የሠራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደኅንነት እና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር እንዳለበት ይገልጻል።

ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ በተደረገላቸው በእነዚህ ሰብአዊ መብቶች ላይ ገደብ በሚጣልበት ጊዜ መብቶችን ለመገደብ የሚያስችል የሕግ መሠረት መኖር (legality)፣ የገደብ እርምጃ የሚወሰደው ቅቡል ዓላማን ለማሳካት ሲሆን (legitimacy)፣ ዓላማውን ለማሳካት የገደቡ አስፈላጊነት (necessity) እና የገደቡን ተመጣጣኝነት (proportionality) መርሆች ሊከተል ይገባል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከእነዚህ ሰብአዊ መብቶች መርሆች አንጻር በባጃጅ የትራንስፖርት ሥራ የተፈጠሩትን ችግሮች በተገቢው ሕጋዊ እርምጃዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በማስተዳደር እና ወደ ሕጋዊ አሠራር እንዲገቡ ማድረግ ሲገባ፣ በጠቅላላ ከተማው ላልተወሰነ ጊዜ ገደብ መጣሉ ከላይ የተገለጹትን ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ የተደረገላቸው መብቶች አደጋ ላይ የጣለ እርምጃ ነው፡፡

በተለይም በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንን እንዲሁም ሴቶች እና ሕፃናትን ታሳቢ በማድረግ እገዳውን ማንሳትና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ መፈለግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

- ኢሰመኮ

Share

Published

Updated

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service