በአፍሪካ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጋር ስላደረጓቸው ውይይቶችና አሜሪካ ስላደረገቻቸው ልዩ ልዩ ድጋፎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን አሜሪካ በፈረንጆቹ 2023 በኢትዮጵያ ለሰብአዊ ዕርዳታ ድጋፍ የሚውል የ331 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ መፍቀዷን ይፋ አድርገዋል። አስታውቀዋል። ድጋፉም በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት [US AID]በኩል እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ ተገናኝተው መምከራቸውንም ገልፀዋል ፡ በስም ማንነታቸውን ባያሳውቁም።
ብሊንከን የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለመፍታት የሠላም ስምምነት ለፈረሙት ሁለቱም ወገኖች አሜሪካ እውቅና እንደምትሰጥና ለተፈፃሚነቱም ሁለቱም አካላት በትኩረት እንዲሰሩ እንዳሰሰቡ አክለዋል።
ብሊንከን እንዳሉት በጦርነቱ የተሳተፈው የኤርትራ ጦር ከአካባቢው እየወጣ መሆኑንም ገልጸዋል።
ስለአጎዋ ዳግም ዕድል ጉዳይ የተጠየቁት ብሊንከን "የሰላም ስምምነቱ ተጠናክሮ ከቀጠለ ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ የገበያ እድል ዳግም መመለስ የምትችልበት እድል ሊኖር ይችላል" ሲሉ ገልጸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ " የሽግግር ፍትህና አገራዊ ምክክሩ" እንዲጠናከር አሜሪካ አስፈላጊውን እርዳታ እንደምታደርግም ተናግረዋል።
[ ደመቀ ከበደ ፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ]