የዓለም ዋንጫ ሊጠናቀቅ አንድ ንጋት ሲቀረው ለሶስተኛ ደረጃ ፍልሚያ በበቁት ቡድናት መካከል በተካሔደው ግጥሚያ ክሮኤሽያ ሞሮኮን በዓል- ራይን ስታዲየም 2 ለ 1 ረትቷል።
ግቦቹን ለክሮኤሽያ ያስቆጠሩት ጆሽኮ ቫርዲዮል ጨዋታው በተጀመረ በ7ኛው ደቂቃ ሲሆን፤ አሽራፍ ዳሪ አስከትሎ በ9ኛው ደቂቃ ለሞሮኮ አቻ ግብ አስቆጥሯል።
ይሁንና ሚስላቭ ኦርቺች በ42ኛው ደቂቃ ለክሮኤሽያ ሁለተኛዋን ግብ ከመረብ ለማዋደደ በመብቃቱና ከሞሮኮ በኩል ለአቻነት የሚያበቃ ግብ ባለመቆጠሩ የግጥሚያው ፍፃሜ ሆኗል።

Badr Benoun of Morocco appaluds the fans following the final whistle of the FIFA World Cup Qatar 2022 3rd Place match between Croatia and Morocco at Khalifa International Stadium on December 17, 2022 in Doha, Qatar. Credit: Youssef Loulidi/Fantasista/Getty Images
ቀሪው 64ኛውና የመጨረሻው ግጥሚያና የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ዛሬ እኩለ ለሊት ይጀምራል።
የፍፃሜ ግጥሚያ ሠንጠረዥ
ፈረንሳይ እና አርጀንቲና (ሰኞ ዲሴምበር 19 / ታሕሳስ 9) 2:00 am [AEDT]