ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 በጀት ዓመት 75.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ዓመት ካገኘው ገቢ ውስጥ ከፍተኛ የሆነው 43.7 በመቶ ገቢ የተገኘው ከድምጽ አገልግሎት ነው። ከዳታና ኢንተርኔት የተገኘው ገቢ 26.6 በመቶ ድርሻ በመያዝ በሁለተኝነት ተቀምጧል።

EtCom.png

Credit: Ethio-Telecom

ተቋሙ ካገኘው ገቢ ውስጥ 18.78 ቢሊዮን ብር የሚሆነው የተጣራ ትርፍ መሆኑም ተገልጿል።

መንግሥታዊው የቴሌኮም አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም ትርፉን ያስታወቀው የተጠናቀቀውን የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን በተመለከተ ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 11፤ 2015 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል እየሰጠ ባለው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም ለጋዜጠኞች ይፋ ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ተቋሙ “ሊድ” የተባለውን ስትራቴጂ የተገበረበት ዓመት መሆኑን አስታውሰዋል።

 በዚህ ስትራቴጂ ትግበራ “ውጤታማ” ተግባራት የተከናወኑበት መሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ፤ በበጀት ዓመቱ 116 አዳዲስ አገልግሎቶች ይፋ መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በ2015 በጀት ዓመትም 75.8 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ያገኘው ይህ ገቢ በእቅድ ተይዞ የነበረው 75.05 ቢሊዮን ብር 101 በመቶ መሆኑን ፍሬሕይወት ጠቅሰዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 ያገኘው ገቢ ከ2014 በጀት ጋር ሲነጻጸር የ23.5 በመቶ ጭማሪ ያለው መሆኑንም አመልክተዋል።

ተቋሙ በ2014 በጀት ዓመት ያገኘው ገቢ 61.3 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡

 እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ገለጻ ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ዓመት ካገኘው ገቢ ውስጥ ከፍተኛ የሆነው 43.7 በመቶ ገቢ የተገኘው ከድምጽ አገልግሎት ነው።

ከዳታና ኢንተርኔት የተገኘው ገቢ ደግሞ 26.6 በመቶ ድርሻ በመያዝ በሁለተኝነት ተቀምጧል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለሌላኛው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ሳፋሪ ኮም ከሚያቀርበው የመሰረተ ልማት ኪራይ 758 ሚሊዮን ብር እንዳገኘ ዛሬ ይፋ የተደረገው የተቋሙ መረጃ ያመለክታል።

 ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ዓመት ካገኘው 75.8 ቢሊዮን ብር ውስጥ 25 በመቶው ትርፍ እንደሆነ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አስታውቀዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተገኘው 18.78 ቢሊዮን ብር ትርፍ፤ ከ2014 ጋር ሲነጻጸር የ109 በመቶ ጭማሪ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል።

 



Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 በጀት ዓመት 75.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ | SBS Amharic