ከዩክሬይን የአገርው ውስጥ ሚኒስትር ጋር አንድ ሕፃንን ጨምሮ የ14 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን፤ የፈረንሳይ ሥሪት የሆነችው ሱፐር ፑማ ሄሊኮፕተር በመዲናይቱ ኪየቭ ክፍለ ከተማ ውስጥ ከሚገኝ አንድ አፀደ ሕፃናት ቅጥር ግቢ ላይ ተከስክሳለች።
በአደጋው በ2021 በፕሬዚደንት ቮሎድሚይር ዘለንስኪ የተሾሙት የአገር ውስጥ ሚኒስትር ዴኒስ ሞናህስቲርስኪ ሕይወት ማለፉን የዩክሬይን ብሔራዊ ፖሊስ ዋን አዛዥ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በሂሊኮፕተር አደጋው የዩክሬይን አንደኛ ተቀዳሚ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር የቭሄኒይ የኒን እና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ፀሐፊ ሕይወትም አልፏል።

Fragments of the helicopter lie on the playground at the site of a helicopter crash on January 18, 2023 in Brovary, Ukraine. Credit: Oleksii Samsonov /Global Images Ukraine via Getty Images
ፕሬዚደንት ዜሌንስኪ በአደጋው ሳቢያ ሕይወታቸውን ላጡት ዩክሬናውያን የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን የገለጡ ሲሆን፤ በተለይም የግልና የቤተሰባቸው በእጅጉ የቅርብ ጓደኛ የነበሩት የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትሩ ዴኒስ ሞናህስቲርስኪ ሞት በእጅጉ ዘልቆ የተሰማቸውና ጎጂ መሆኑን ተናግረዋል።