በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ አስተናጋጅነት ሐምሌ 14 ተጀምሮ ዛሬ ነሐሴ 14 የተጠናቀቀው የ2023 የፊፋ የሴቶች ዓለም ዋንጫ በስፔይን አሸናፊነት በሲድኒ አውስትራሊያ ስታዲየም ተጠናቅቋል።
ስፔይን እንግሊዝን 1 ለ 0 አሸንፋ ለዓለም ሻምፒዮናነት ያበቃቻን ግብ በ29ኛው ደቂቃ መረብ ላይ ያሳረፈችው ኦልጋ ካርሞና ናት።
ከ1991 አንስቶ እስከ 2023 ለዘጠኝ ጊዜያት በተካሔደው የሴቶች እግር ኳስ የዓለም ዋንጫ ዩናይትድ ስቴትስ ለአራት ጊዜያት (1991፣ 1999፣ 2015፣ 2019)፣ ጀርመን (2003፣ 2007) ኖርዌይ (2015) ጃፓን (2011) እና ስፔይን (2023) ለሻምፒዮናነት በቅተዋል።
በዕለቱ በተካደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት የ19 ዓመቷ የስፔይን ተጫዋቿ ሳልማ ፐሬሉዌሎ የምርጥ ወጣት ተጫዋች ዋንጫ ወስዳለች።

Salma Paralluelo. Credit: Justin Setterfield/Getty Images

Mary Earps. Credit: Quinn Rooney/Getty Images

Aitana Bonmati. Credit: SAEED KHAN/AFP via Getty Images
ድል አድራጊዋ ስፔይን የወርቅ ሜዳልና የ2023 የፊፋ ዓለም ዋንጫ በእጇ አስገብታለች።

Ivana Andres of Spain lifts the FIFA Women's World Cup Trophy following victory in the FIFA Women's World Cup Australia & New Zealand 2023 Final match between Spain and England at Stadium Australia on August 20, 2023, in Sydney, Australia. Credit: Justin Setterfield/Getty Images

England players line up on the podium at the award ceremony following the FIFA Women's World Cup Australia & New Zealand 2023 Final match between Spain and England at Stadium Australia on August 20, 2023, in Sydney, Australia. Credit: Quinn Rooney/Getty Images