የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ለሁለት ሐኪሞች የሕይወት ዘመን ሽልማት ሰጠ

ማኅበሩ ከሕይወት ዘመን ሽልማት በተጨማሪ ዶክተር ትህትና ንጉሴን በሴት ወጣት ተጽዕኖ ፈጣሪ ሐኪም፤ እንዲሁም ዶክተር ፈቀደ አግዋርን በወንድ ወጣት ተጽዕኖ ፈጣሪ ሐኪም ዘርፍ ሸልሟል።

EMA.jpg

Credit: PR

የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር በ59ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤው ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለሰጡ ሁለት ሐኪሞች የህይወት ዘመን ሽልማትን አበረከተ።

ዶክተር ይርጉ ገብረህይወት በወንድ ጾታ እንዲሁም ዶክተር ተቋም ደበበ ደግሞ በሴት የህይወት ዘመን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ተሸላሚዎቹ በ ሙያቸው የተሻለ የሕክምና አገልግሎት እንደሰጡ በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ማህበሩ ከህይወት ዘመን ሽልማት በተጨማሪ ዶክተር ትህትና ንጉሴን በሴት ወጣት ተጽዕኖ ፈጣሪ ሐኪም በሚል ሲሸልም ዶክተር ፈቀደ አግዋርን ደግሞ በወንድ ወጣት ተጽዕኖ ፈጣሪ ሐኪም በማለት ሸልሟል።

አዲስ ህይወት የማገገሚያ ማዕከል ደግሞ የዓመቱ ምርጥ የጤና ተቋም በሚል ዕውቅና ተሰጥቶታል።

ሽልማቱን የጤና ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ተግባር ይግዛው ሰጥተዋል።

Share

Published

Updated

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service