የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዝ ትረስ ከ44 ቀናት በኋላ ስልጣናቨውን ለመልቀቅ ግድ ተሰኝተዋል። ይህም በእንግሊዝ ታሪክ ለአጭር ጊዜ በመሪነት የቆዩ መሪ አድርጓቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከስልጣን እንደሚለቁ ለንጉሥ ቻርልስ ማስታወቃቸውን አካትተው ሁለት ደቂቃ ያልሞላ ንግግር አድርገው ከጋዜጠኞች ጥያቄ ሳይቀበሉ ወደ ቢሮአቸው ተመልሰዋል።
ተኪያቸውም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በወግ አጥባቂው ፓርቲ እንደሚመረጥ ይጠበቃል።
ዛሬና ነገ ከወግ አጥባቂው ፓርቲ የምክር ቤት አባላት ውስጥ ሊዝ ትረስን ለመተካት ዕጩዎች ይቀርባሉ።
ይህም እንግሊዝ በአራት ወራት ውስጥ ሶስተኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሰየም ግድ ትሰኛለች።