በቡዳፔሽት-ሃንጋሪ ከኦገስት 19 / ነሐሴ 13 አንስቶ በመካሔድ ላይ ያለው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወንዶች 10000 ሜትሮች ሩጫ ውድድር ኡጋንዳ፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ለአሸናፊነት በቅተዋል።

በእዚህም መሠረት፤
- ጆሽዋ ቼፕቴጌይ 27:51.42 የወርቅ ሜዳል
- ዳንኤል ሲሚዩ 27:52.6 የብር ሜዳል
- ሰለሞን ባረጋ 27:52.72 የነሐስ ሜዳል ሲያገኙ፤
- ብርሃኑ አረጋዊ ውድድሩን በ27:55.71 አራተኛ ሆኖ ጨርሷል።
Share

