የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜለንስኪና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁለቱ አገራት ግንኙነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነ የስልክ ንግግር አድርገዋል።
ንግግራቸው ያተኮረውም የሩስያ ከጥቁር ባሕር የእህል አቅርቦት ተነሳሽነት መውጣት፣ የባሕር ቀዘፋን መግታት፣ የዩክሬይን ወደብና የኃይል መሠረተ ልማት ላይ የቦምብ ድብደባ ማካሔድ ላይ እንደነበር የዩክሬይን ፕሬዚደንታዊ ጽሕፈት ቤት ገልጧል።
አቶ ዜሌንስኪ፤ በስልክ ንግግሩ ወቅት በዩክሬይንና በአፍሪካ አገራት መካከል የንግግር መድረኮችን መፍጠር እንደሚያሻ ያነሱት ሲሆን፤ አያይዘውም "የኢትዮጵያ ድምፅ፣ የአፍሪካ ሕብረት ድምፅ፣ የመላው አፍሪካ ድምፅ ለእኛ ጠቃሚ ነው" ብለዋል።
ሁለቱ መሪዎች ሉላዊ የሰላም ጉባኤ በማዘጋጀት ላይ እንደመከሩና ፕሬዚደንት ዜለንስሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዩክሬይንን እንዲጎበኙ የጋበዙ መሆኑን የፕሬዚደንቱ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
የዓለም ዋንጫ
ትናንት በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ የጋራ አስተናጋጅነት ሲድኒ ላይ በተካሔደው የሴቶች ዓለም ዋንጫ መክፈቻ ግጥሚያ አውስትራሊያ አየርላንድን በፍፁም ቅጣት ምት በተገኘች ግብ 1 - 0 ስታሸንፍ ኒውዝላንድ ኦክላንድ በተደረገው ግጥሚያ ኖርዌይን በተመሳሳይ ውጤት 1 - 0 ረታለች።

Steph Catley of Australia (centre) celebrates with teammates after scoring a penalty during their opening match of the 2023 FIFA Women's World Cup against Ireland in Sydney on Thursday night. Credit: AAP / Dan Himbrechts
የአውስትራሊያ ቀጣዩን ግጥሚያ ከናይጄሪያ ጋር ብሪስበን ላይ ሐሙስ ጁላይ 27 / ሐምሌ 20 ታካሂዳለች።