ምርጫ 2022፤ በመላ አውስትራሊያ ድምፅ መስጠት ተጀምሯል

*** የሌበር መሪ አንቶኒ አልባኒዚ "እንደዚህ ጠቅላይ ሚኒስትር [ስኮት ሞሪሰን] ያለ በጣሙን ከፋፋይ አይቼ አላውቅም" አሉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን በርካታ በርካታ የሊብራል ምክር ቤት ወንበሮችን ለመንጠቅ ተቃርበውና ስጋት ሆነውባቸው ያሉትን የግለ ተመራጮች አስመልክተው "ለግል ተወዳዳሪዎች ድምፅ መስጠት ትርምስ ለበዛበት ፓርላማና ደካማ መንግሥት ድምፅ መስጠት" እንደሚሆን አሳሰቡ።

2022 Federal Election

Opposition leader Anthony Albanese (L) and Prime Minister Scott Morrison (R). Source: SBS

የአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ዛሬ እየተካሔደ ባለው አገር አቀፍ የምርጫ ቀን በመላ አውስትራሊያ ሁሉንም 7000 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች መክፈት መቻሉን አስታወቀ። 

ኮሚሽኑ አክሎም ድምፅ ለመስጠት መመዘኛዎችን ከሚያሟሉ አውስትራሊያውን ውስጥ ከግማሽ በላይ በቅድመ ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች፣ በፖስታና በስልክ አገልግሎቶች ድምፅ መስጠታቸውን ገልጧል።  

የሌበርና ሊብራል መሪዎች በመጨረሻው የምርጫ ዘመቻ አተያያቸውን አንፀባርቀዋል። 

የሌበር መሪ አንቶኒ አልባኒዚ "ሜዲኬይርን ለማጠንከር፣ የሙዋዕለ ሕፃናት ወጪን ዋጋ ለመቀነስ፣ በርካታ ነገሮችን አውስትራሊያ ውስጥ ለመፈብረክ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ እርምጃ ለመውሰድ፣ ብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለማቆምና አገሪቱን ወደ አንድነት ለማምጣት ያሉንን ዕቅዶች ይፋ አድርገናል"

"እንደዚህ ጠቅላይ ሚኒስትር ያለ በጣሙን ከፋፋይ አይቼ አላውቅም" 

"አገሪቱን አንድ የማድረጊያ መንገድ ለነባር ዜጎች የፓርላማ ድምፅ ማስገኘት ነው" ብለዋል።
2022 Federal Election
Australian Opposition leader Anthony Albanese and partner Labor candidate for the seat of Higgings Michelle Ananda-Rajah Source: AAP
አቶ አልባኒዚ ለዝቅተኛ ደመውዝ ተከፋዮች በሰዓት የአንድ ዶላር ጭማሪ መደረግ አንዳለበት ዳግም አንስተዋል። 

የጠቅላይ ሚኒስትሩንም ፈቃደኝነት አላማሳየት አመላክተው ነቀፋን ሰንዝረዋል። 
 
መጪው ጊዜ የተሻለ እንዲሆንም መራጮች ድምፃቸውን ለሌበር ፓርቲ እንዲሰጡ ጠይቀዋል። 
 
በሌላም በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን መራጮች ለተሻለ ምጣኔ ሃብት መንግሥታቸውን ዳግም እንዲመርጡ ጥሪ አቅርበዋል። 
 
ለአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የፓርላማ ድምፅ ለመስጠት ለጊዜው አብላጫ ስምምነት እንደሌለና ወቅቱ ሲደርስ ዕውን እንደሚሆን ተናግረዋል። 
Waziri Mkuu Scott Morrison, akiwa katika kampeni ya uchaguzi mkuu
Prime Minister Scott Morrison with how to vote cards at the Laurimar Primary School on federal election day in Doreen, the seat of McEwen in Melbourne’s north. Source: AAP
አያይዘውም በርካታ የሊብራል ምክር ቤት ወንበሮችን ለመንጠቅ ተቃርበውና ስጋት ሆነውባቸው ያሉትን የግለ ተመራጮች አስመልክተው "ለግለ ተመራጮች ድምፅ መስጠት ማለት ትርምስ ለተመላበት ፓርላማ ድምፅ መስጠትና ትልቅ ውዥቀት ባለበት በአሁኑ ወቅት መንግሥት በየዕለቱ ለሕልውናው እንዲደራደር መዳረግ ነው። የአውስትራሊያን ፓርላማና መንግሥት ደካማ ያደርጋሉ" ብለዋል። 
 
የግል ተወዳዳሪዎች በአብዛኛው ዋነኛ የምርጫ ዘመቻ አጀንዳዎቻቸው አድርገው ያሉት የአየር ንብረት ለውጥና ጥርስ ያለው የፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዲቋቋም ማድረግ ናቸው። 
 
ተወዳዳሪዎችና የምርጫ ውጤት
 
በዛሬው አገራዊ ምርጫ አውስትራሊያ በዘጠኝ ዓመታት ውስጥ ስድስተኛ ጠቅላይ ሚኒስትሯን ለመንበረ ስልጣን ታበቃለች ተብሎ ይጠበቃል። 


151 ወንበሮች ላሉት የአውስትራሊያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1203 ዕጩዎች ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል።


ለ40 የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት 421 ዕጩዎች ክፍለ አገራትና ግዛቶችን ወክለው ይፎካከራሉ።


ድምፅ መስጠት ዛሬ አመሻሽ ላይ 6pm ሲሆን ያበቃል።
 
ቀደም ብለው የመረጡትን ከአምስት ሚሊየን በላይ ድምፆች ጨምሮ ከ17 ሚሊየን በላይ መራጮች ድምፅ ይቆጠራል።


በአሁኑ ወቅት የሞሪሰን መንግሥት በአዲሱ አወቃቀር ሳቢያ በምዕራብ አውስትራሊያ ይዞት የነበረው አንድ ወንበር ሲቀነስ 75 የምክር ቤት ወንበሮችን ይዞ ይገኛል።
 
የሌበር ፓርቲ አሁን ይዟቸው ያሉትን 68 የምክር ቤት ወንበሮችና በአዲሱ አወቃቀር ቪክቶሪያ ውስጥ ያገኘውን አንድ ወንበር አክሎ 69 ወንበሮችን ይዟል። 


አሸናፊ ፓርቲ ራሱን ችሎ መንግሥት ለማቆም 76 የምክር ቤት ወንበሮችን ማሸነፍ ይጠበቅበታል። 


የሌበር ፓርቲ ከራሱ የቀጥታ ድምፅ 36 ፐርሰንትና የሌሎች ፓርቲዎች ታካይ ተመራጭ ድምፆችን አክሎ በ 53.5 ፐርሰንት የሊብራል/ናሽናልስ ጥምረትን እየመራ ሲሆን፤ ይህም በመራጮች ድምፅ አሰጣጥ ዕውን ከሆነ 83 የምክር ቤት ወንበሮችን ሊያሸንፍ እንደሚችል የሕዝብ አስተያየት ስብስቦች ያመለክታሉ። 





Share

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service