አንቶኒ አልባኒዚ ለዘጠኝ ዓመታት በመንግሥትነት የቆየውን የሊብራል/ናሽናልስ ጥምር መንግሥት ድል ከነሱ በኋላ ባደረጉት ንግግር አውስትራሊያውያንን ወደ አንድነት ለማምጣት ቃል ገቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ትንናት ቅዳሜ ምሽት መንግሥታቸው በሌበር ፓርቲ ድል መነሳቱን አምነው ተቀብለዋል። ከሊብራል ፓርቲ መነሳታቸውንም ገልጠዋል።
የሌበር ፓርቲ 77 የምክር ቤት ወንበሮችን ሊብራል/ናሽናልስ 59 ግሪንስ ፓርቲን ጨምሮ የግል ተወዳዳሪዎች 15 ወንበሮችን እንደሚያገኙ የስሌት ትንበያ አለ።
እንዲያም ሆኖ ምናልባትም ሌበር ፓርቲ ራሱን ችሎ 76 ወንበሮችን በማሸነፍ መንግሥት ለማቆም ሊሳነውም ይችላል።
ይሁንና እስካሁን በአውስትራሊያ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ውጤት ሌበር 73 ሊብራል/ናሽናልስ 51 ግሪንስ ፓርቲን ጨምሮ የግል ተወዳዳሪዎች 12 የምክር ቤት ወንበሮችን አሸንፈዋል።
ሊብራል ፓርቲ
የጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንን ሽንፈት ተከትሎ የሊብራል ፓርቲ መሪነት ሥፍራ ተኪ ስለሚሻ ምናልባትም የሊብራል ፓርቲ መሪ ለመሆን ደጋግመው ሙከራ ያደረጉት ፒተር ዳተን ቀጣዩ የሊብራልና ተቃዋሚ ቡድን መሪ ይሆናሉ የሚሉ አተያዮች እየተንሸራሸሩ ነው።
የወደፊት የሊብራል ፓርቲ መሪ ሲልም በለስ የቀናቸው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ በፓርቲያቸው ዘንድ ይነገርላቸው የነበሩት በጅሮንድ ጆሽ ፍራይደንበርግ በግል ተወዳዳሪዋ ሞኒክ ራያን በ10 ፐርሰንት ተበልጠው የምክር ቤት ወንበራቸውን እንደሚያጡ ታምኗል።

Former Australian Defence minister Peter Dutton. Source: Getty
ግሪንስ ፓርቲ
የግሪንስ ፓርቲ በዘንድሮው አገር አቀፍ ምርጫ ሁለት ተጨማሪ የሕዝብ ምክር ቤት ወንበሮችን ኩዊንስላንድ ውስጥ በሊብራል ስር የነበረውን ሪድ እና በሌበር ተይዞ የነበረውን ግሪፊዝ በማሸነፍ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።
እስካሁን በተካሔደ ቆጠራ ብሪስበን - ኩዊንስላንድ፣ ማክናማራ - ቪክቶሪያ እና ሪችመንድ - ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ ወደ ግሪንስ አዝምመው ይገኛሉ።
ELEX INDEPENDENTS
Zoe Daniel and Allegra Spender are each set to claim House of Representatives seats as independent candidates prepare to hugely impact the next parliament.
Treasurer Josh Frydenberg is facing a strong challenge from Monique Ryan in Kooyong, in Victoria, where more than half the vote has been counted.
In New South Wales, independent Kylea Tink has taken the seat from Liberal MP Trent Zimmerman in North Sydney, while Sophie Scamps leads Jason Falinski in Mackellar.
Independent MP Zali Steggall, who is set to hold onto her seat of Warringah, said last night the swing away from the coalition especially on the issue of climate change was clear to see.
[["The feedback very much was people are really frustrated, cost of living issues, but also climate change simply did not feature in the policies and the platforms from the major parties and in particular from Scott Morrison. It's like he forgot that over the last three years we were ravaged by bushfires and floods and somehow that was swept under the carpet.]]