ዝነኛው ቀልደኛ፣ ተዋናይና ደራሲ ባሪ ሃምፍሬስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ባለፈው ሳምንት እስከ 20 ሺህ የሚገመቱ ሱዳናውያን ለፍልሰት ተዳርገዋል

Barry Humphries .jpg

Barry Humphries (L), and "Dame Edna Everage / Barry Humphries" (R). Credit: Ian Jacobs/WireImage / Don Arnold/WireImage

ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ በ89 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ዝነኛው ቀልደኛ፣ ተዋናይና ደራሲ ባሪ ሃምፍሬስ የተሰማቸው ጥልቅ ሐዘን ገለጡ።

 ሃምፍሬስ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሕክምና እያገኙ በነበረበት የሲድኒ ቅዱስ ቪንሰንት ሆስፒታል ቤተሰባቸው ከአጠጋባቸው ተገኝተው ሳለ ነው።

ቤተሰቦቻቸው ቅዳሜ ምሽት ባወጡት መግለጫ "እስከ ሕይወቱ ፍፃሜ ድረስ ራሱን ሆኖ እንዳለ ነበር፤ ድንቅ አዕምሮው የጥበብና ቸርነት መንፈሱን አልሳተም ነበር" ብለዋል።

አቶ አልበኒዚ "ሃምፍሬስ ከዴም ኤድና እስከ ሳንዲ ስቶን የከዋክብት ገፀ ባሕሪያት አዝናንቶናል፤ ሁሌም ግና የከዋክብቱ ብሩህ ኮከብ ባሪ ነው" ብለዋል።

አክለውም፤ ሃምፍሬስን ታላቅ ጥበበኛ፣ ቀልደኛ፣ ደራሲ፣ ባለ ስጦታና ስጦታን ሰጪ ሲሉ ገልጠዋቸዋል።  

ተዋናይ ሃምፍሬስ የዴም ኤድና ኢቨሬጅን የሴት ገፀ ባሕሪይ በመጫወት ለበርካታ አሠርት ዓመታት ተውነዋል።

ሱዳን

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድርጅት በሱዳን መከላከያ ሠራዊትና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መካከል እየተካሔደ ባለው ፍልሚያ ሳቢያ የሱዳናውያን ስደተኞች ማዕበል ወደ ቻድ እየጎረፈ መሆኑን አስታወቀ።

ባለፈው ሳምንት በካርቱምና በተወሰነው የአገሪቱ ክፍል እየተካሔደ ካለው ግጭት በመሸሽ ከ10,000 እስከ 20,000 የሚደርሱ ሱዳናውያን ስደተኞች ወደ ቻድ ፈልሰው መዝለቃቸው ተገምቷል።

በቻድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ኃላፊ ፓይሪ ሆኖራት አዲሶቹ ፍለሰተኞች ቀደም ሲል ከሱዳን ሸሽተው ቻድ ባሉት 400,000 ስደተኞች ላይ ተጨማሪ መሆናቸውንና አብዛኛዎቹም ሕፃናትና ሴቶች እንደሆኑ አመልክተዋል።

አያይዘውም፤ ምንም እንኳ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድርጅት እስከ 100 ሺህ ስደተኞችን ለማስተናገድ ዝግጁ ቢሆንም የፍልሰተኞቹ ቁጥር ግና ከዚያ ሊበልጥ እንደሚችል ግምታቸውን አሳድረዋል።

 



 









Share

Published

By Kassahun Seboqa Negewo, NACA
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service