በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና ውጪ "ሲመተ ጳጳሳት" ተከናውኗል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች በቅሬታ አሳሰቡ

መንግሥት ክስተቱን አስመልክቶ ሕጋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ሲሉም ጥሪ አቀረቡ።

EOTC.jpg

Credit: Minasse Wondimu Hailu/Anadolu Agency/Getty Images

ሕጋዊነት ያልተከተለ "ሲመተ ጳጳሳት" ተከናውኗል በሚል መግለጫውን የሰጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

ቅዱስነታቸው እሑድ ማለዳ የተሰማው "ሲመተ ጳጳሳት" ጉዳይ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ መሆኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዢን ቀርበው አመልክተዋል።

ክስተቱንም አስመልክቶ ለሊቃነ ጳጳሳት፣ መንግሥትና ምዕመናን ጥሪ ቀርቧል።

በጥሪውም፤ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ፣ መንግሥት ክስተቱ በአገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣና. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት እንዲጠብቁ ሲሉ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ይህ በእንዲህ አንዳለም፤ ከቅዱስ ሲኖዶሱ ይሁንታ ውጪ 26 “ኤጲስ ቆጶሳት” ሲመተ ጵጵስና መፈጸማቸውን ለሲመተ ጳጳሳት ክንዋኔው ኃላፊነቱን የወሰዱት ጳጳሳት አስታውቀዋል።

ይህንኑ እርምጃ ለመውስውድ ግድ የተሰኙትም የቤተክርስቲያኒቱ የጎሳና ቋንቋ አመዳደብ ሚዛናዊነት ወደ አንድ ጎን ያደላ በመሆኑ እንደሁ ገልጠዋል።

ሁነቱን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የማኅበረ ቅዱሳን ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ “በተፈፀመው ድርጊት ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶናል። ድርጊቱ በቤተክርስቲያን ታሪክ ከታዩት አስዛኝ መከፋፈሎች ሁሉ የተለየ ነው” ሲል ገልጦ አባቶች አስቸኳይ መፍትሔ እንዲያበጁለት አሳስቧል።

ለተከሰተው ልዩነት እልባት ለማበጀት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አስተዳደር ጉባኤ በመወያያት ላይ መሆኑ ተገልጿል።



Share

Published

Updated

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service