ስዊድንና ደቡብ አፍሪካ ባካሔዱት የምድብ ግጥሚያ 2 ለ 1 ተለያይተዋል።
በግጥሚያው የመጀመሪያዋን ግብ በ48ኛው ደቂቃ ላይ በሂልዳ ሞጋና አማካይነት ያስቆጠረችው ደቡብ አፍሪካ ናት።

ሆኖም ስዊድን በፍራይዶሊና ሮልፎ የአቻ ግብ አግቢነት በ65ኛዋ ደቂቃ እንዲሁም፤ አማንዳ ኢሌስቴድት በ90ኛዋ ደቂቃ ሁለተኛዋን ግብ በማስቆጠር ለድል በቅታለች።
አሁን ለመጠናቀቅ እየተቃረበ ባለው ግጥሚያ ኔዘርላንድስ ፖርቱጋልን 1 ለ ባዶ እየመራች ሲሆን፤ ከሁለት ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ፈረንሳይና ጃማይካ ይጋጠማሉ።
በነገው ዕለት ከቀትር በፊት ጣልያን ከአርጀንቲና፣ ብራዚል ከፓናማ ሲጫወቱ፤ አመሻሹ ላይ ጀርመንና ሞሮኮ ይጋጠማሉ።

