"ጎሰኝነት ኑፋቄ ነው"የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ "ሲመተ ጳጳሳት" ያከናወኑ ሿሚና ተሿሚዎች ደመወዝ እንዲታገድና የሚገለገሉባቸው ቢሮዎችና ማረፊያ ቤቶች በአግባቡ እንዲጠበቁ ትዕዛዝ አስተላለፈ።

A parishioner of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.jpg

A parishioner of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church. Credit: J. Countess/Getty Images

ጉባኤው ድርጊቱን "በቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመ ሁሉን አቀፍ ክህደት" ሲል አውግዟል። አያይዞም "ክህደቱን የፈጸሙት አካላት ሥልጣን የሰጣቸውን መዋቅር (ተቋም) በመካድ የፈጸሙት ድርጊት እጅጉን አሳዛኝ ነው" ብሏል።

የተፈጸመው ጉዳይም "ሕገ ወጥና ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ወንጀል ነው" ያለው የአስተዳደር ጉባኤ "በምንም መመዘኛ ይህን ከፈጸሙ አካላት ጋር መደራደር በተዘዋዋሪ የቤተክርስቲያናችንን ሕግና ሥርዓትን ማፍረስ ነው" ሲልም አስታውቋል።

በማያያዝም ጎሰኝነት ኑፋቄ መሆኑን የገለጸው አስተዳደር ጉባኤው፤ ይህን በመሰለ ተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙ ክህደቶች በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ተነቅፏል ካለ በኃላ በቋንቋ መማርና ማስተማር ችግር እንዳልሆነ በመረዳት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያስተምሩ አባቶችን በመሾም አገልግሎት እንዲሰጡ ስታደርግ መቆየቷን ሕገ ወጥ ድርጊቱን ከፈጸሙ አካላት በላይ ማስረጃ አይኖርም ብሏል።

ጉባኤው ለቅዱስ ሲኖዶስ የውሳኔ አካል ሊሆኑ የሚችሉ የውሳኔ ሀሳቦችን ከቀኖና ቤተክርስቲያን እና ከሕግ አንጻር በመነሳት የጠቆመ ሲሆን፤ የተፈጸመው ክህደት ከቀኖና ቤተክርስቲያንና ከሕግ አንጻር እንዴት እንደሚገለጽ የሚያመለክት ሰፊ የሚዲያ ሥራ እንዲሰራ በመወሰንና በቂ ማብራሪያ የሚሰጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን በመመደብ ከጥር 14 ጀምሮ ሁሉም ቋንቋዎች ማብራሪያ እንዲሰጥ ወስኗል።

ኹሉም የቤተክርስቲያኗ መዋቅር ተቋማቱን በንቃት መጠበቅና ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚተላለፍ መመሪያን በትጋት መጠበቅ እንደሚገባና አስፈላጊው መመሪያ በአስቸኳይ እንዲተላለፍ የወሰነው አስተዳደር ጉባኤው በቤተክርስቲያን ላይ ክህደት የፈጸሙ አካላት ወይም የሿሚና ተሿሚ ነን ባዮች ደመወዝ እንዲታገድና የሚገለገሉባቸው ቢሮዎችና ማረፊያ ቤቶች በአግባቡ እንዲጠበቁ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፤ መንግሥትም እያደረገ ያለውን የቤተክርስቲያናትን ጥበቃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጉባኤው ጠይቋል።

ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ምዕመናንና ምዕመናት ከጸሎት በተጨማሪ መዋቅራዊ መመሪያዎችን በትዕግስት እንዲጠብቁ አደራ በማለት የዕለቱን ስብሰባ በጸሎት ማጠናቀቁን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለጠቅላይ ቤተክሕነት አስተዳደር ጉባኤ የከረረ መግለጫ አስባብ የሆኑት አካላት ቀደም ሲል የ26 “ኤጲስ ቆጶሳት” ሲመተ ጵጵስና መፈጸማቸውን ጳጳሳት አስታውቀዋል።

ይህንኑ እርምጃ ለመውስውድ ግድ የተሰኙትም የቤተክርስቲያኒቱ የጎሳና ቋንቋ አመዳደብ ሚዛናዊነት ወደ አንድ ጎን ያደላ በመሆኑ እንደሁ ገልጠዋል።



Share

Published

By Stringer Report
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service