ያለፉትን አራት ዓመታት በእሥር ላይ ያሳለፉት የቀድሞው የኢሕአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ በረከት ስምኦን ከእስር የተፈቱት ዛሬ ረቡዕ ጥር 17 ቀን 2015 ነው።
አቶ በረከት ከነበሩበት ባሕር ዳር እስር ቤት የተፈቱት “የአመክሮ ጊዜያቸውን ጨርሰው” መሆኑን ተገልጿል።
አቶ በረከት ከጥረት ኮርፖሬሽን የገንዝብ ብክነት ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው ክስ፤ የስድስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
ከባሕር ዳር ተነስተው አዲስ አበባ መግባታቸውም ታውቋል።