የበጀት 2022-23 ተጠቃሚዎችና ተጎጂዎች

የአውስትራሊያ ፌዴራል በጅሮንድ ጂም ቻልመርስ የ2022-23 በጀት አቅርበዋል። በጀቱ የ$36.9 ተረፈ ፈሰስ ጉድለት አሳይቷል። በ2026 የአውስትራሊያ የተጣራ ዕዳ $766 ቢሊየን፤ የዋጋ ግሽበት እስከሚቀጥለው ዓመት 8 ፐርሰንት ሊደርስ ይችላል።

Treasurer Jim Chalmers.jpg

Treasurer Jim Chalmers speaks during a budget lockup press conference to announce details of the 2022-23 federal budget to the media at Parliament House on October 25, 2022 in Canberra, Australia. Credit: Martin Ollman/Getty Images

ተጠቃሚዎች

  • ከመንግሥት ጋር በሽርካ ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው አዲስ ቤት ገዢዎች (በሁለት ዓመት ውስጥ)
  • የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ (ከ2004 ጀምሮ አንድ ሚሊየን የሽርካ ቤቶች ግንባታ)
  • ቤተሰብና ቤተሰብ ለመመስረት ዕሳቤ ላይ ያሉ (የወሊድ ፈቃድና ክፍያ ከ2026፣ የሙዋዕለ ሕፃናት ክፍያ ቅነሳ ከመጪው ጁላይ 1 ጀምሮ)
  • መሠረተ ልማት (ሜልበርን፣ ኩዊንስላንድ ብሩስ አውራ ጎዳና፣ ከሲድኒ ኒውካስትል ፈጣን ባቡር $8.1 ቢሊየን ዶላር)
  • የTAFE እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች (480,000 ነፃ የTAFE ኮሌጅ ሥፍራዎች 20,000 የዩኒቨርሲቲ ሥፍራዎች)
  • የአየር ንብረት ለውጥ ($25 ቢሊየን እስከ 2030)
  • የኤለኢክትሪክ መኪና ገዢዎች (አሠሪዎች $9000 ግለሰቦች $4700 የግብር ቅናሽ በዓመት)
  • ብሔራዊ ብሮድባንድ በይነመረብ (በ2025 መጨረሻ ግድም ለ15 ሚሊየን መኖሪያዎች ፋይበር ዝግጁ አገልግሎት ሥራ ማስኪያጃ $2.4 ቢሊየን)
  • የአረጋውያን ክብካቤ አገልግሎት ሰጪዎች ($2.5 ቢሊየን)
  • አረጋውያን ላጤና ጥንዶች (የ$70 ሚሊየን ጭማሪ)
  • ለሴቶች ደኅንነት ($170 ሚሊየን ድጎማ)
  • የግብረ አካል ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው ($437.4 ሚሊየን በመጪዎቹ ሶስት ዓመታት)
  • የፓስፊክ ደሴቶች (3000 ቪዛዎች)
Treasurer Jim Chalmers.jpg
Treasurer Jim Chalmers delivers the 2022-23 Federal Budget in the House of Representatives at Parliament House on October 25, 2022 in Canberra, Australia. Credit: Getty Images

ተጎጂዎች

  • የኤሌክትሪክና የጋዝ ዋጋ ከፋዮች (የኤሌክትሪክ ዋጋ በገና በዓል ዋዜማ በ20 ፐርሰንት፤ 30 ፐርሰንት በሚቀጥለው የፋይናንስ ዓመት ጭማሪ። የጋዝ ዋጋ በሚቀጥሉት 18 ወራት በ44 ፐርሰንት ጭማሪ ያሳያል )
  • ሆስፒታሎች (የኮቪድ - 19 ድጎማ አይራዘምም)
  • ግብር በአግባቡ የማይከፍሉ ኩባንያዎችና ግለሰቦች (በታክስ ቢሮ በኩል በአራት ዓመት ውስጥ እስከ $4.7 ቢሊየን ለመሰብሰብ ታቅዷል)
  • የግል አማካሪዎች (በመጪዎቹ አራት ዓመታት ውስጥ ለመንግሥት የ$3.6 ቢሊየን ወጪ ቁጠባ ዕቅድ)
  • ወንጀለኞች (ከጃኑዋሪ 1 ጀምሮ የፌዴራል ወንጀል መቀጮ ከ$222 ወደ $275 ከፍ ይላል፤ ከዚያም በየሶስት ዓመት ይጨምራል)
  • ጠቅላይ እንደራሴ (በቀድሞው መንግሥት ለወደፊት መሪዎች ፎረም ተመድቦላቸው የነበረ $16 ሚሊየን ተቀንሷል)

2 min read

Published

Updated

By Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now

የበጀት 2022-23 ተጠቃሚዎችና ተጎጂዎች | SBS Amharic