በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሓት መካከል ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 15 ደቡብ አፍሪካ ውስት የተጀመረው የሰላም ንግግር እሑድ እንደሚያበቃ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል አቀባይ ማስታወቃቸውን ሮይተርስ አመልክቷል።
የፕሬዚደንቱ ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ የደቡብ አፍሪካ ሚና አስተናጋጅነትና እርዳታ ሰጪነት መሆኑንም አያይዘው ገልጠዋል።
የሰላም ንግገሩ የሚካሔደው በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነትን ነው።