SKIP TO MAIN CONTENT

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና ቴዎድሮስ አስፋው በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲወጡ ታዘዘ

ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው።

Dawit Begashaw.jpg
Journalist Dawit Begashaw. Credit: D.Begashaw

1 min read

Published

By Stringer Report

Source: SBS


Skip to article content
የቀድሞው የ“አል አይን ኒውስ” ጋዜጠኛ እንዲሁም “አራት ኪሎ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ሁለቱም በ20,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ታዟል፡፡
ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው።
 ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ሐሙስ ሚያዚያ 5/2015 ቂሊንጦ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ማክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ፖሊስ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን የሚታወስ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ሚያዚያ 4/2015 ምሽት ላይ ባህርዳር ከሚገኘው "ሆምላንድ ሆቴል" በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱ ይታወሳል።


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Stream now