የሲቪል መብቶች ተሟጋች የነበሩት የማልከም-ኤክስ ሴት ልጅ የአባቷን አሟሟት አስመልክታ በኤፍ.ቢ.አይ፣ ሲ.አይ.ኤ እና የኒውዮርክ ከተማ ፖሊስ ላይ ክስ ልትመሠርት መነሳቷን አስታወቀች።
አፍሪካዊ - አሜሪካናዊው ማልከም ኤክስ እ.አ.አ. ፌብሪዋሪ 21,1965 ኒውዮርክ ከተማ ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ በ58 ዓመታቸው በጥይት ሕይወታቸው አልፏል።
በማልከም ኤክስ ግድያ በስህተት ተጠርጥረው የነበሩት መሐመድ አዚዝና ካሊል ኢስላም በ2021 ውነጀላቸው ተነስቶላቸዋል።
የማልከም ኤክስ ሴት ልጅ ኢልያሳህ ሻባዝ የአባታቸው ግድያ ከስለላና ሕግ አስከባሪ ድርጅቶች ጋር ተያይዥነት ስለመኖርና አለመኖሩ እውነታ እሳቸው፣ ቤተሰባቸውና ተከታዮቻቸው ማወቅ እንደሚሹ፣ የክስ ስሚውም ለጥያቄዎቻቸው ምላሾችን እንደሚያስገኙና ለአባታቸውም የሚገባቸውን ፍትህ ያስገኛል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናገረዋል።
ጉዳዩን አስመልክቶ እስካሁን ከኤፍ.ቢ.አይ፣ ሲ.አይ.ኤ እና የኒውዮርክ ከተማ ፖሊስ የተሰጠ ምላሽ የለም።
የናይጄሪያ ብሔራዊ ምርጫ 2023
በአማፂ እስላማዊ ቡድናት፣ እገታ፣ ግጭት እያመሳትና፣ የጥሬ ገንዘብ፣ ነዳጅና የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት፣ ስር የሰደደ ሙስናና ድህነት አውኳት ያለችው ናይጄሪያ መራጮች ለአገር አቀፉ ምርጫ ድምፆቻቸውን ሰጥተዋል።
ይሁንና በርካታ መራጮች በተጓተተው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት፣ መራጮችን መስፈራራትና ቴክኒካዊ እክሎችን አስመልክተው ብስጭታቸውን ገልጠዋል።
ለስምንት ዓመታት ስልጣን ላይ ቆየተው ተሰናባች የሆኑትን የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ማሃማዱ ቡሃሪን በአዲስ ፕሬዚደንት ለመተካትና የተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ለመምረጥ የተከናወነው ብሔራዊ ምርጫ ውጤት ተጠቃሎ ይፋ ለመሆን እስከ ማክሰኞ የቆጠራ ጊዜን ግድ እንደሚል ተነግሯል።