Watch FIFA World Cup 2026™

LIVE, FREE and EXCLUSIVE

የቡድን 20 ፋይናንስ ሚኒስትሮች የዩክሬይን ጦርነትን አስመልክቶ የጋራ መግለጫ ለማውጣት ከስምምነት ላይ ሳይደርሱ ቀሩ

የዩክሬይን ፕሬዚደንት አውስትራሊያ ኤምባሲዋን ዳግም እንድትከፍት ጥሪ አቀረቡ

Ukrainian President Volodymyr Zelensky speaks to the media during a press conference in Kyiv.jpg

Ukrainian President Volodymyr Zelensky speaks to the media during a press conference in Kyiv. Credit: EPA / SERGEY DOLZHENKO/EPA

የቡድን 20 ሚኒስትሮች የዩክሬይንን ጦርነት በአንድ ድምፅ በመግለጥ ላይ ሳይስማሙ ቀሩ።

የዓለም ግዙፍ የምጣኔ ሃብት አገራት ሚኒስትሮች ስብሰባ የተካሔደው በሕንድ አስተናጋጅነት ሲሆን፤ ከሩስያና ቻይና በገጠመው ተቃውሞ ሳቢያ ከስምምነት ላይ መድረስ ሳይችል ቀርቶ አክትሟል።  

ባለፈው ወርኃ ኖቬምበር ባሊ-ኢንዶኔዥያ የተካሔደው የቡድን 20 የመሪዎች ስብሰባ ግጭቱ በውዥቀት ላይ ያለውን የዓለም ምጣኔ ሃብት ለባሰ ሁኔታ ሊዳርግ እንደሚችል በማሳሰብ በብርቱ አውግዞ ነበር።

ይሁንና የሕንድ ፋይናንስ ሚኒስትር ኒርማላ ሲታራማን በአሁኑ ወቅት ከጋራ ስምምነት ላይ የደረሰ መግለጫ ማውጣት እንደማይቻል አመላክተው፤ በምትኩ የጉባኤው ሰብሳቢን ማጠቃለያና ከጋራ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ የሚያመላክት ሰነድን ይፋ ማድረግ አማራጭ ስለመሆኑ አስታውቀዋል።  

የአውስትራሊያ ኤምባሲ በዩክሬይን

የአውስትራሊያ ፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን አውስትራሊያ የኪየቭ ኤምባሲዋን ዳግም በመክፈቱ ላይ እንድታስብበት አሳሰበ።

የተቃዋሚ ቡድኑ ማሳሰቢያ መነሾ የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከSBS የኤምባሲውን መዘጋት አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፤ አውስትራሊያ የኪየቭ ኤምባሲዋን ዳግም በመክፈት ዲፕሎማሲያዊ ውክልናዋን እንድትቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው።

 

 

I


1 min read

Published

By NACA, Kassahun Seboqa Negewo

Source: SBS


Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps

Watch on SBS

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service

Watch now