በሚሊየን የሚቆጠሩ የቪክቶሪያ መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተመሙ ነው

የቆዳ ካንሰር ግንዝቤን ለማስጨበጥ በሚል ዕሳቤ ቢሺህዎች የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን ራቁታቸውን በሲድኒ የቦንዳይ የባሕር ዳርቻ ፎቶግራፎችን ተነሱ።

VIC State Election.jpg

A Kim Jong Un impersonator running for a seat in Parliament known as 'Howard X' at Albany Rise Primary School in the seat of Mulgrave on November 26, 2022 in Melbourne, Australia. Victoria went to the polls on Saturday, with the incumbent Labor government of Daniel Andrews leading Matthew Guy's Liberals by a wide margin in pre-election surveys. Credit: Asanka Ratnayake/Getty Images

ከሚሊየን በላይ የቪክቶሪያ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት የክፍለ አገር መንግሥት ለማቋም ድምፃቸውን እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

ውጤቱም ለሶስተኛ ጊዜ ለመመረጥ በተወዳዳሪነት የቀረበውን የፕሪሚየር አንድሩስ ሌበር መንግሥትን ወይም በማቲው ጋይ የሚመራውን የተቃዋሚ ቡድን ለቀጣዩ አራት ዓመታት ስልጣን ላይ የሚያስቀምጥ ይሆናል።

የምርጫ ጣቢያዎች በመላው ቪክቶሪያ ከ 8am ጀምሮ ክፍት የሆኑ ሲሆን 6pm ላይ ይዘጋሉ።

የቪክቶሪያ የምርጫ ኮሚሽን ለመምረጥ ብቁ ከሆኑ ነዋሪዎች ውስጥ ገሚሶቹ ከዛሬው ዋነኛ የምርጫ ቀን በፊት ድምፃቸውን እንደሰጡ ግምት አሳድሯል። .

 የክፍለ አገሩ የጤና ሥርዓትን ማጎልበት፣ ለኑሮ ውድነት ብልሃትን ማበጀትና ለክፍለ ከተማና አካባቢ የባቡር መገናኛ መስመሮች ተጨማሪ ድጎማን ማድረግ የሌበር፣ የቅንጅቱና የግሪንስ ፓርቲዎች ዋነኛ የምርጫ መቀስቀሻ አጀንዳዎች ነበሩ።

ፕሪሚየር ዳንኤል አንድሩስ ከኔትዎርክ ዘጠኝ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ
የምርጫ ጣቢያዎቹ እስከሚዘጉ ድረስ የምረጡን ቅስቀሳቸውን እንደማያቋረጡ፣ ነፃ የአፀደ ሕፃናት አገልግሎት፣ ነፃ የቴፍ ኮሌጅ ኮርሶችን መጨመር፣ ታዳሽ ኃይል ማጎልበት፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን ለትርፍ ሳይሆን ለሕዝብ ጠቀሜታ ማዋልን ተቀዳሚ አጀንዳዎቻቸው በማድረግ እንደሚቀሉ ተናግረዋል።

በሌላም በኩል የሊብራልና ናሽናልስ ፓርቲ ቅንጅት መሪ ማቲው ጋይ በበኩላቸው፤ መራጮች የእሳቸውን ቅንጅት በመምረጥ የጤና ሥርዓቱን ለመጠገን፣ ለኑሮ ውድነት ብልሃት ለማበጀት እንዲያስችሏቸው በኔትዎርክ ዘጠኝ በኩል ጠይቀዋል።

ሌበር ተቃዋሚ ቡድኑን 54.5 ፐርሰንት ለ 45.5 ፐርሰንት በሆነ የሕዝብ አስተያየት ስብስብ እየመራ ሲሆን፤ ቅንጅቱ ለመንግሥትነት ራሱን ለማብቃት አሁን ባሉት 27 የምክር ቤት ወንበሮች ላይ 18 ተጨማሪ ወንበሮችን ማሸነፍ ግድ ይሰኛል።

የራቁት ፎቶግራፍ

በፎቶግራፍ ዓለም ሁነኛ ሥፍራ ያላቸው ፎቶግራፍ አንሺ ስፔንሰር ቱኒክ የቆዳ ካንሰርን አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስጨበጥ 2500 ሰዎችን ገናና በሆነው የሲድኒ ቦንዳይ ባሕር ዳርቻ ራቁታቸውን ሆነው ፎቶግራፎችን አንስተዋል።

አቶ ቱኒክ ኩነቱን በተመለከተ ለ SBS ሲገልጡ 'ታላቅ ስኬት' ብለውታል።  

Share

Published

Updated

By NACA, Kassahun Seboqa Negewo
Source: SBS

Share this with family and friends


Follow SBS Amharic

Download our apps
SBS Audio
SBS On Demand

Listen to our podcasts
Independent news and stories connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians.
Ease into the English language and Australian culture. We make learning English convenient, fun and practical.
Get the latest with our exclusive in-language podcasts on your favourite podcast apps.

Watch on SBS
SBS World News

SBS World News

Take a global view with Australia's most comprehensive world news service
በሚሊየን የሚቆጠሩ የቪክቶሪያ መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች እየተመሙ ነው | SBS Amharic